Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የቀድሞው የአሜሪካ የኢራን ጉዳዮች ልዩ መልክተኛ ሮበርት ማሌይ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት፣ ትራምፕ በቴህራን ላይ ምንም ያህል "ጫና" ቢያሳድሩም፣ ኢራን "መብቴ ነው" የምትለውን የዩራኒየም ማበልጸግ ፕሮግራም አሳልፋ አትሰጥም።

ልዩ መልክተኛው የኢራንን አቋም ሲያብራሩ፣ "እንደገና መታለል አይፈልጉም፤ እንዲሁም የራሳቸው የሆነ ክብር እና እሴት አላቸው" ብለዋል። አክለውም፣ ይህ የኢራናውያን አቋም በከፍተኛ የኢኮኖሚም ሆነ የወታደራዊ ጫና ውስጥ እንኳን ቢሆን "ሊጠፋ የማይችል ነገር ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.