በሆርሙዝ ሰርጥ የሚያቋርጡ መርከቦች ቁጥር ከ100 ወደ 6 አሽቆልቁሏል
****************
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
በአሜሪካ እና ኢራን ግጭት ምክንያት በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የሚያልፉ መርከቦች ቁጥር በ95 በመቶ መቀነሱን አናዶሉ ዘግቧል።
ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በዚህ ስትራቴጂያዊ የባህር መስመር በቀን በአማካይ 100 መርከቦች ያልፉ ነበር።
ከጦርነቱ መጀመት ወዲህ ግን ይህ ቁጥር ወደ 6 ዝቅ ብሏል፤ ይህም ቀደም ሲል ከነበረው እንቅስቃሴ ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ ነው።
በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት የመርከቦቹ እንቅስቃሴ መጠነኛ መሻሻል አሳይቶ በቀን ከ20 እስከ 25 መርከቦች ማለፍ መጀመራቸውን የኢራን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ለዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ወሳኝ መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት እና በቀጣናው ያለው የጸጥታ ስጋት፣ መርከቦች አማራጭ መንገዶችን እንዲፈልጉ እና ጉዟቸውን እንዲያቋርጡ እያደረጋቸው ይገኛል።
የቀጣናው ውጥረት በቶሎ የማይረግብ ከሆነና የሆርሙዝ ሰርጥ ዝግ ሆኖ ከዘለቀ በዓለም አቀፍ የንግድ ሰንሰለት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል የብዙዎች ስጋት ነው።
በቢታኒያ ሲሳይ
#middleeast #hormuz #fuel #ebc #ethiopia

2 months ago