Logo
SeledaPost
ፓይለቱ በበራራ ላይ እያለ  የልብ ህመም አጋጠመው

ባለፈው አርብ ​ከቴነሪፍ ወደ በርሚንግሃም 220 ተጓዦችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው የጄት2 (Jet2 LS1266) በረራ፣ ዋናው አብራሪ በድንገት በደረሰባቸው የልብ ህመም ምክንያት በፖርቶ፣ ፖርቱጋል አስቸኳይ ማረፊያ ለማድረግ ተገዷል ሲል ሜትሮ ዘግቧል።

​በበረራው ወቅት የረዳት አብራሪው አይሮፕላኑን ለመቆጣጠር ከፍታ በፍጥነት በቀነሰበት ወቅት ተጓዦች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወድቀው ነበር።

የበረራ አስተናጋጆች እያለቀሱ በህክምና የሰለጠነ ሰው ይፈልጉ እንደነበር ተገልጿል።

​አይሮፕላኑ በፖርቶ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም ያረፈ ሲሆን፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ለአብራሪው አስቸኳይ ህክምና አድርገውላቸዋል።

ተሳፋሪዎች ግን ያለምንም ማረፊያ ለአውሮፕላን ሰራተኞቹ ያላቸውን አጋርነት እየገለጹ፣ ለአስራ ሶስት ሰዓታት በአውሮፕላን ማረፊያው ለመቆየት መገደዳቸውን  ተናግረዋል።

Seledadotio
Seledadotio
11 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.