Logo
EBC
ውጤቱ ባይቀናም ተስፋው አልደበዘዘም - የቀይ ቀበሮዎቹ ታዳጊዎች ለዓለም ዋንጫ ያደረጉት አስደናቂ ጉዞ በሞዛምቢክ ተገትቷል
*****************

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ያደረገው የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በሞዛምቢክ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

አሚር ሚስባህ ኢትዮጵያን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ ቢያስቆጥርም ሞዛምቢክ በዲያጎ ኤሌምቤ አቻ መሆን ችላለች።

ውጤቱን ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች ወደ መለያ ምት ያመሩ ሲሆን ሞዛምቢክ 5 ለ 4 አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ታዳጊዎች በሞሮኮ በተካሄደው የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ጀምሮ ባሳዩት ብቃት የብዙዎችን ልብ ማሸነፍ ችለዋል።

ልጆቻችን ዛሬ ባይሳካላቸውም ነገ ብሩህ ጊዜ እንዳላቸው ከወዲሁ አሳይተውናል።
#ebc #ethiopia #football #worldcup

12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.