በሰሜን ሸዋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ለብልፅግና ፓርቲ የድጋፍና የቅስቀሳ ሰልፎች ተካሄዱ
****************
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች "በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ፤ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ሀሳብ በርካታ ወጣቶች የተሳተፉባቸው የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍና የጎዳና ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሰልፎች ተካሂደዋል።
እነዚህ የድጋፍ ሰልፎች በዞኑ ስር በሚገኙ በጣርማበር፣ አሳግርት እና አንጾኪያ ገምዛ ወረዳዎች የተከናወኑ ሲሆን የየአካባቢው ወጣቶች በነቂስ በመውጣት ለፓርቲው ያላቸውን አጋርነት በተግባር አሳይተዋል።
ሰልፈኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት መጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሀዊ፣ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው መህለጻቸውን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
በተጨማሪም ወጣቶች ያለምንም ችግር ድምጻቸውን በመስጠትና በምርጫው ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ኢትዮጵያን የማሻገርና የማጽናት ታሪካዊ አደራቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
#ethiopianelection2026 #ethiopianbroadcastingcorporation

14 days ago