Logo
EBC
ኢትዮጵያዊያን አዳጊዎች በዓለም አቀፉ የአዳጊዎች ሮቦቲክስ ውድድር በሕዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ አሸነፉ
**********************

የኢትዮጵያ አዳጊዎች ልዑክ በዓለም አቀፉ የአዳጊዎች የሮቦቲክስ እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ሻምፒዮና በመሳተፍ በሕዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ 1ኛ በመሆን አሸንፏል።

በሚቺጋን አሜሪካ ሎውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የ2026 የ‘ሮቦፌስት’ ዓለም አቀፍ የአዳጊዎች የሮቦቲክስ እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት ሻምፒዮና ኢትዮጵያዊያን ተወዳዳሪዎች አስደናቂ ድሎችን አስመዝግበዋል።

ልጆቻችን ከ39 የቴክኖሎጂ ኃያላን ሀገራት ከተወጣጡ 738 ቡድኖች ጋር በመፎካከር ነው በተለያዩ ዘርፎች ማሸነፍ የቻሉት።

በውድድሩ በሕዝብ ምርጫ ሽልማት ዘርፍ ኢትዮጵያውያን አዳጊዎች ቀዳሚ በመሆን ሲያሸንፉ፣ በሕክምና ሮቦቲክስ ዘርፍ 5ኛ እንዲሁም በፈጠራ ማሳያ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከአንድ ወር በፊት በግሪክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ሚኖአን ሮቦቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያውያን አዳጊዎች 2ኛ ደረጃን በማግኘት የሀገራቸውን ስም ማስጠራታቸው ይታወሳል።
#ebc #ethiopia #robotics #robofest2026 #ai

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.