ውብ አዲስ ፪ የሥዕል ኤግዚቢሽን ተመረቀ
#ethiopia | በሠዓሊ ሀሮን ሱለይማን የተዘጋጀው ውብ አዲስ ፪ የሥዕል ትርዒት በጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።
ኤግዚቢሽኑን መርቀው የከፈቱት የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሉባባ ጀማል እና ታዋቂው ሠዓሊና መምህር ጋሽ እሸቱ ጥሩነህ ናቸው።
የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ከዝግጅቱ በስተጀርባ በትብብር በመሥራት ድጋፍ አድርጓል።
ይህ የኪነጥበብ ዝግጅት ከግንቦት 07 እስከ ግንቦት 23 ቀን ድረስ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ፍላጎት ያላቸው ማናቸውም የጥበብ አፍቃሪያን ያለ ምንም የመግቢያ ክፍያ መታደም ይችላሉ።
የሥዕል ትርዒቱ የሚገኝበት ስፍራ በፒያሳ አድዋ ሙዚየም አጠገብ በሚገኘው የጣይቱ ማዕከል ነው።
#art #artexhibition #painting #piazza #culture #addisababa #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

18 days ago