የጋዜጠኛና ደራሲ ስመኝ ግዛው አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል
#ethiopia | ለዛ ባላቸው ጽሁፎቿ የምትታወቀው ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ ስመኝ ግዛው የእናቴ "ሮሚዮ" እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች የተሰኘ አዲስ መጽሐፏን ለገበያ ልታቀርብ መሆኑን ገልጻለች።
የእናቴ "ሮሚዮ" መጽሐፍ ተራ የሚመስሉ ነገር ግን ጥልቅ ትርጉም ያላቸውን የሕይወት ክስተቶች በረቂቅ አጻጻፍ የሚያስቃኙ 20 አጫጭር ታሪኮችን በውስጡ አካትቷል።
ታሪኮቹ በእውነተኛ የፍቅርና የትዳር ሕይወት ውጣ ውረዶች ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን ስሜትን በሚነኩ ግጥሞችም የታጀቡ መሆናቸውን ደራሲዋ አስታውቃለች።
በ 220 ገጾች ተቀንብቦ የቀረበው ይህ ሥራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ ግምገማ የተደረገበት ሲሆን መጽሐፉ በሳል ይዘትና ልዩ አቀራረብ እንዳለው ምሁሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
የመጽሐፍ ምርቃቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደሚከናወንም ታውቋል።
#የእናቴሮሚዮ #ስመኝግዛው #አዲስመጽሐፍ #ስነጽሁፍ #ኢትዮጵያ #አጫጭርታሪኮች #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago