(ዘ-ሐበሻ ዜና) የብሪክስ ሚኒስትሮች በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ልዩነት በመፍጠራቸው የጋራ መግለጫ ሳያወጡ ቀሩ፡፡ የብሪክስ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኒውዴልሂ ያደረጉትን የ2 ቀናት ዛሬ አጠናቀዋል፡፡ እንዲህ አይነት ስብሰባዎች ሲከናወኑ በመጨረሻው ቀን የጋራ መግለጫ የሚወጣ ቢሆንም የብሪክስ ሚኒስትሮች ግን ይህንን አላደረጉም፡፡ የስብሰባው አስተናጋጅ ህንድ እንደገለፀችው የጋራ መግለጫ ሊወጣ ያልቻለው በመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ ላይ ‹‹አንዳንድ አገራት የተለየ ሀሳብ በማንፀባረቃቸው›› ነው፡፡
ህንድ በመግለጫዋ አባል አገራቱ በመካከለኛው ምስራቅ ሉአላዊነት፣ የባህር ደህንነትና የሲቪል መሰረተ ልማቶች ጥበቃና የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት ጨምሮ ‹‹የየራሳቸውን ብሄራዊ አቋምና የተለየ አመለካከት ገልፀዋል›› ያለች ሲሆን በዚህም የጋራ መግለጫው ሊወጣ እንዳልቻለ አስረድታለች፡፡
በተጨማሪም አንድ አባል አገር በቀይ ባህር በባብኤል መንደብ ወሽመጥና በጋዛ ደህንነት ዙሪያ በተዘጋጀው የጋራ መግለጫ ላይ ቅሬታውን ማቅረቡንም አስታውቃለች፡፡ የብሪክስ አባል አገራት ብራዚል፣ ህንድ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ዩናይትድ አረብ ኤመሬትስና ኢንዶኔዥያ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በብሪክስ ውስጥ ከተሰባሰቡት ከእነዚህ አገራት መካከል በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ኢራንና ናይትድ አረብ ኤመሬትስ ከፍተኛ ልዩነት ያላቸው መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

3 months ago