Logo
Getu Temesgen
1 ሺህ 139 የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኞች በስነምግባር ጥሰት ተቀጡ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሥነ ምግባር ጉድለትና ብልሹ አሠራር በፈጸሙ 1 ሺህ 139 ሠራተኞቹ ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን መውሰዱን አስታወቀ።

እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል 16 ሠራተኞች ከሥራ የተሰናበቱ ሲሆን 721 የሚሆኑት ደግሞ የደሞዝ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። ቀሪዎቹ 402 ሠራተኞች የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

ከተወሰዱት እርምጃዎች ውስጥ 103ቱ ከደንበኞች በደረሱ ጥቆማዎች መሠረት የተከናወኑ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 1 ሺህ 36 ጉዳዮች በተቋሙ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት የተደረሰባቸው ናቸው።

ተቋሙ የሙስና መጠቆሚያ መተግበሪያንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ከደንበኞች የደረሱትን 427 ጥቆማዎች መመርመሩን ገልጿል።

በዚህም መሠረት በደንበኞች ጥቆማ ምክንያት 7 ሠራተኞች ከሥራ የተሰናበቱ ሲሆን 80 የደሞዝ ቅጣት፣ 14 የጽሑፍ ማስጠንቀቂያና 2 ከኃላፊነት የማንሳት እርምጃዎች ተፈጽመዋል።

አገልግሎቱ የብልሹ አሠራር ጥቆማዎች ከሚቀርቡባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል የአዲስ ቆጣሪ ጥያቄ፣ የኃይል መቆራረጥ፣ የጥገና መዘግየት፣ የቆጣሪ ንባብና የቢል አሰባሰብ እንዲሁም የንብረት አያያዝ እንደሚገኙበት ጠቅሷል።

ደንበኞች በድረ ገጽ (www.eeuethics.et) አማካኝነት ጥቆማዎችን እንዲሰጡ ያበረታታው ተቋሙ፣ ለጠቋሚዎች አስፈላጊውን ጥበቃና እውቅና እንደሚሰጥም አረጋግጧል።

ይህም አሠራር ተቋሙ ብልሹ አሠራሮችን ለመታገል ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #ሙስና #አስተዳደራዊእርምጃ #መልካምአስተዳደር #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.