አክሱም- ከታሪክ ማህደር እስከ ቅድስና ማማ
አክሱም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ብቻ ሳይሆን ለመላው ክርስትና አለም ልዩ ስፍራ ያላት ከተማ ናት።
የቃል ኪዳኑ ታቦት ማረፊያ፣ የቅዱስ ያሬድ ዜማ መፍለቂያ እና የመጀመሪያው የክርስትና መንግስት ማዕከል መሆኗ ለከተማዋ የ"ቅዱስ ከተማነት" መንፈሳዊ ትርጉም ይሰጣታል።
አንድን ከተማ "ቅዱስ" የሚያሰኘው በውስጧ የያዘቻቸው መንፈሳዊ ቅርሶች እና የተከናወኑ ታላላቅ ሃይማኖታዊ ክስተቶች ናቸው።
*ኢየሩሳሌም (እስራኤል) ለክርስቲያኖች፣ ለአይሁድና ለሙስሊሞች ቅዱስ ናት።
* ቫቲካን (ሮም) ለካቶሊክ እምነት ተከታዮች የቅድስና ማዕከል ናት።
* መካና መዲና (ሳውዲ አረቢያ): ለሙስሊሞች እጅግ የተቀደሱ ስፍራዎች ናቸው።
አክሱምም በተመሳሳይ መልኩ ከ3 ሺህ ዓመታት በላይ የዘለቀ የሃይማኖት ታሪክ ያላት፣ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መገኛ በመሆኗ "ቅዱስ" ተብላ መጠራቷ ከታሪካዊ እውነታው ጋር የተጣጣመ ነው።
ይህ ስያሜ አዲስ ማንነትን መፍጠር ሳይሆን የነበረውን ጥንታዊ ክብር በይፋ እውቅና መስጠት ነው።
በአለማችን ላይ መካ "ቅዱስ ከተማ" (The Holy City of Mecca) ተብላ መጠራቷን ማንም አይቃወምም። ይህ መብትና ክብር ለሌሎች ሃይማኖታዊ ማዕከላትም ሊሰጥ ይገባል።
አንድ ሙስሊም መካን ቅዱስ አድርጎ እንደሚያከብር ሁሉ የክርስትና እምነት ተከታይም አክሱምን ቅዱስ አድርጎ የመጥራት መብት አለው። አንዱን "ቅዱስ" ብሎ ተቀብሎ ሌላውን "አይገባውም" ማለት አመክንዮአዊ ግድፈት ከመሆኑም በላይ ሃይማኖታዊ እኩልነትንና መከባበርን የሚሸረሽር "double standard" ነው።
ሰላምና አብሮነት የሚጸናው እያንዳንዱ እምነት ለሌላው የሚሰጠውን ክብርና ስያሜ በፀጋ ሲቀበል ብቻ ነው።
ይህ ስያሜ ከሃይማኖታዊ ትርጉሙ ባለፈ ለከተማዋና ለነዋሪዎቿ (ለክርስትያኑም ሆነ ለሙስሊሙ) ግዙፍ የኢኮኖሚ ዕድል ይዞ ይመጣል አክሱም "ቅዱስ ከተማ" ተብላ በአለም አቀፍ ደረጃ ስትታወቅ
እንደ ቫቲካንና መካ ሁሉ አክሱምም የአለም ክርስቲያኖች የንግደት ስፍራ (Pilgrimage site) ትሆናለች። ይህ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ የውጭ ቱሪስቶችን ይስባል።
ቱሪስቶች ሲመጡ ሆቴል ያርፋሉ፣ ምግብ ይበላሉ፣ በትራንስፖርት ይንቀሳቀሳሉ፣ ቅርሳቅርስ ይገዛሉ በዚህ ሰንሰለት ውስጥ በአክሱምና በአካባቢው የሚኖሩ ሙስሊም ነጋዴዎች ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ናቸው።
በንግድ ስራ ላይ በስፋት የሚታወቁት የእስልምና እምነት ተከታዮች የቱሪስቶችን ፍላጎት የሚያሟሉ አገልግሎቶችን በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ማሳደግ ይችላሉ።
ከተማዋ የ"ቅዱስ ከተማ" ደረጃ ስታገኝ መንገዶች፣ አውሮፕላን ማረፊያዎችና የውሃና መብራት አገልግሎቶች ይሻሻላሉ። ይህ ልማት ደግሞ ሃይማኖት ሳይለይ ለሁሉም ነዋሪ የኑሮ ጥራት መሻሻል ምክንያት ይሆናል።
አክሱምን ቅዱስ ከተማ ብሎ መሰየም ታሪካዊ ፍትህ ከመሆኑም በላይ ለቀጣናው ሰላምና የኢኮኖሚ ብልጽግና ትልቅ ፋይዳ አለው ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ይህንን ስያሜ በጋራ የመኖር እሴት እና እንደ ትልቅ የቱሪስት ገቢ ምንጭ አድርገው ሊመለከቱት ይገባል።
መካ ለሙስሊሞች ያላትን ክብር ሳንነካ አክሱምም ለክርስቲያኖች ያላትን ስፍራ እውቅና መስጠት መቻቻልን ያጎለብታል።
አክሱም በቅድስናዋ ከፍ ስትል የምትታወቀው ኢትዮጵያ ናት ተጠቃሚውም የሃገሪቱ ህዝብ በሙሉ ነው። ስለዚህ ይህንን ውሳኔ በፀጋ ተቀብሎ ለጋራ ዕድገት መጠቀም ብልህነት ነው ይህ ማለት ግን የሙስሊሙ ማህበረሰብን መብት ባከበረ እና ጥያቂያቸውን ( እንደ የቀብር ቦታ መስጊድ እና ሌሎች .. ) ከከተማ አቅራቢያ የሚመልስ የመፍትሄ ሃሳብን በመስጠት ነው
በሳውዲ አረቢያ የሚገኙት መካ እና መዲና እጅግ ጥብቅ የሆነ ሕግ አላቸው።
በእነዚህ ከተሞች ውስጥ ከእስልምና ውጪ ያሉ ሌሎች የሃይማኖት ተቋማት (አብያተ ክርስቲያናት፣ ቤተ መቅደሶች፣ ወዘተ) እንዳይገነቡ በሕግ ተከልክሏል።
ምክኒያቱ ደግሞ ከተሞቹ ለሙስሊሞች ብቻ የተከለሉ (Exclusive) እና የሃይማኖቱ መንፈሳዊ ማዕከል ተደርገው ስለሚወሰዱ ነው።
እንዲያውም ሙስሊም ያልሆነ ሰው ወደ መካ ከተማ መግባት እንኳ በሕግ አይፈቀድለትም።
ቫቲካን በዓለም ላይ ካሉ ትናንሽ ሀገራት አንዷ ስትሆን መላው ሀገሪቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ግዛት ናት።
በቫቲካን ግዛት ውስጥ የሌላ እምነት ተቋም መገንባት አይፈቀድም።
ቫቲካን ራሷን የቻለች ሀገር ብትሆንም በዙሪያዋ ባለው የሮም ከተማ (ጣሊያን) ውስጥ ግን የሌሎች እምነቶች ተቋማት (መስጂዶችን ጨምሮ) በነፃነት ይገነባሉ።
ኢየሩሳሌም ለሦስቱም ታላላቅ ሃይማኖቶች (ክርስትና፣ እስልምና እና አይሁድ) "ቅዱስ ከተማ" ናት።
እጅግ ጥንታዊ በሆነው የከተማዋ ክፍል (Old City) ውስጥ አብያተ ክርስቲያናት መስጂዶችና ምኩራቦች ጎን ለጎን ተከባብረው ይገኛሉ።
አዳዲስ ግንባታዎች ላይ ጥብቅ የታሪክ ጥበቃ ቁጥጥር ቢኖርም የሌላ እምነት ተቋም አይገነባም የሚል ፍጹም ክልከላ የለም።

26 days ago