የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ፕሮጀክት ፍሪደም' ዘመቻ የሆርሙዝ ሰርጥን ያስከፍት ይሆን?
***************
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን በመዝጋቷ ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ ለተጣለባቸው መርከቦች አሜሪካ ሽፋን በመስጠት እርዳታ እንደምታደርግ አስታውቀው ነበር።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ይህንን አዲስ ዘመቻ ይፋ ካደረጉ በኋላ ውጊያዎች ዳግም የተጀመሩ መስሏል። አሜሪካ በርካታ የኢራን ጀልባዎችን መምታቷን ስትገልጽ ኢራን በበኩሏ ተከታታይ ጥቃቶችን መሰንዘሯ ተነግሯል።
የሆርሙዝ ሰርጥን አሁንም በቁጥጥሯ ስር እንዳለ የምትገልፀው ኢራን አዲስ የሰላም ዕቅድ ለአሜሪካ ማቅረቧን ብታስታውቅም በስፍራው የሚታየው ውጥረት ግን እንደቀጠለ ነው።
የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዘም ጋሪባባዲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት በዘላቂነት ለመቋጨት የሚያስችል አዲስ እና ሁሉን አቀፍ የሰላም ዕቅድ በፓኪስታን በኩል ለአሜሪካ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል።
ጋሪባባዲ "አሁን ኳሷ በአሜሪካ ሜዳ ላይ ናት፤ ዋሽንግተን በዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እና በግጭት ቀጣይነት መካከል መምረጥ ይኖርባታል" ሲሉ ገልጸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ፕሬዚዳንቱ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ሀገራት በሆርሙዝ ሰርጥ የታገቱ መርከቦቻቸውን ነፃ ለማውጣት እንዲረዱዋቸው እንደጠየቋቸው ገልፀው አሜሪካ ምላሽ ለመስጠት መርከቦቹን ከእነዚህ በኢራን የተከለከሉ የውሃ መስመሮች በሰላም ትመራቸዋለች ብለዋል።
በዚህ ንግግር የኢራን ምላሽ በማንኛውም ሁኔታ በሰርጡ በኩል የሚደረግ የደህንነት ጉዞ ከኢራን ጋር መተባበር አለበት በማለት የኢራኑ ሜጀር ጄኔራል አሊ አብዶላሂ የተናገሩ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራቅቺ በበኩላቸው ፕሮጀክት ፍሪደም የውጥረት ፕሮጀክት ነው ሲሉ ገልጸውታል።
እንደ ዓለም አቀፉ የባህር ላይ ድርጅት (IMO) መረጃ ከሆነ ከኢራን ጋር ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ 20 ሺህ መርከበኞች እና 2 ሺህ መርከቦች በባህረ ሰላጤው ውስጥ ታግተው ይገኛሉ።
Ethiopian Broadcasting Corporation #hormuzstrait #hormuz

1 month ago