አርሰናል ከአትሌቲኮ ማድሪድ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናግዳል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በታሪካቸው አንድም ጊዜ ማሳካት ያልቻሉት ሁለቱም ቡድኖች ወደ ፍጻሜው ለማለፍ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
በኦፕታ ቅድመ ትንበያ መሰረት ለዋንጫው ቀዳሚውን ግምት ያገኘው አርሰናል እና ከቀሩት አራት ቡድኖች ዝቅተኛውን ቅድመ ግምት ያገኘው አትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ነው፡፡
በሪያድ ኤር ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በተደረገው የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሩት ግብ 1 አቻ በሆነ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ለዋንጫው ቅድመ ግምት በማግኘት ቀዳሚው ክለብ ቢሆንም ተጋጣሚው አትሌቲኮ ማድሪድ ብርቱ ተፎካካሪ መሆኑን በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ አሳይቷል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በታሪኩ ማሸነፍ ያልቻለው አርሰናል ለፍጻሜ መድረስ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን ወቅቱም በፈረንጆቹ 2006 ነበር፡፡
አርሰናል ከፈረንጆቹ 2006 በኋላ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ መድረክ የፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በዛሬው ጨዋታ የሚያደርገው ፉክክር ይጠበቃል፡፡
በ2024/25 የውድድር ዓመት በመድረኩ እስከ ግማሽ ፍጻሜ የተጓዝ አርሰናል በዚህ የውድድር ዘመን በሻምፒየንስ ሊጉ የሚያደርገው ጉዞ ተጠባቂ ነው፡፡
በአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ የሚመራው አትሌቲኮ ማድሪድ በበኩሉ በታሪኩ ሦስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ላይ መገኘት መቻሉ ይታወሳል፡፡
አትሌቲኮ ማድሪድ በተለያዩ ጊዜያት በመድረኩ ፍጻሜ ላይ መድረስ ቢችልም ዋንጫውን ግን አንድም ጊዜ ማንሳት አልቻለም፡፡
አትሌቲኮ ማድሪድ ለመጨረሻ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ የሆነው በፈረንጆቹ 2016 እንደነበር አይዘነጋም፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ለማሳካት በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎ ለፍጻሜ ለመድረስ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
ለዚህም በሳምንቱ መጨረሻ በተደረገው የስፔን ላሊጋ ጨዋታ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ ለአብዛኛው የቡድኑ ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋቾች እረፍት ሰጥተዋል፡፡
የአትሌቲኮ ማድሪድ የፊት መስመር ተጫዋች ዩሊያን አልቫሬዝ ለጨዋታው ብቁ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ካይ ሃቨርትዝ እና ጁሪየን ቲምበር በአርሰናል በኩል በጉዳት ለጨዋታው የማይደርሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
በኢምሬትስ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ጀርመናዊው ዳኛ ዳንኤል ሴበርት በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡
የሁለቱ ቡድኖች የድምር ውጤት አሸናፊ በነገው ዕለት ጨዋታቸውን ከሚያደርጉት ባየርን ሙኒክ እና ፒኤስጂ ድምር ውጤት አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይገናኛል፡፡
በአቤል ነዋይ

1 month ago