Logo
EBC
እንዲህ በትብብር ስንሠራ ወደ ብልጽግና የሚያሻግሩ ተግባራትን ማሳካት እንችላለን - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
******************

እንደ ፈለገ ጊዮን ኢኮ ሪዞርት ያሉ ግዙፍ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች ለክልሉ ተጨማሪ ጸጋ ከመሆናቸውም በላይ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ስለመሆናቸው የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ።

በባህር ዳር ከተማ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ ሪዞርቱ ጥራት፣ ውበትና ምቾትን ከመላበሱ ባሻገር፣ ለታሪካዊው የጣና ሐይቅ ደህንነት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመገንባቱ ለሌሎች መሰል ፕሮጀክቶች እንደ አርአያ የሚጠቀስ መሆኑን አብራርተዋል።

ሪዞርቱ ከመንግሥትና ከግል ባለሀብቱ ጥንካሬ የተገኘ የጋራ ውጤት መሆኑን በመጥቀስ፣ "ሀሳብና ተግባር ሲገናኙ የማይታለፉ የሚመስሉ ፈታኝ ጊዜያትን በትብብር መሻገር እንደሚቻል የታየበት ነው ብለዋል።

ሪዞርቱ ለጎብኚዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ከዘርፉ ማግኘት የሚገባንን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማግኘት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ገልጸዋል።

እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ፥ የጣና ሐይቅ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ መገለጫ እንደመሆኑ፣ አሁን ላይ ተግባራዊ እየሆነ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ደግሞ ዛሬን ከነገ በማገናኘት የቱሪዝም ሀብቶቻችንን ለትውልድ በሚተርፍ መልኩ ለማልማት ዕድል ፈጥሯል።

እንዲህ በትብብር ሲሥሠራ ወደ ብልጽግና የሚያሻግሩ ተግባራትን ማሳካት እንደሚቻል በመጠቆም፣ ዛሬም ሆነ ነገ ትብብራችንን በማጠናከር ለትውልድ የሚተርፍ አሻራ ማኖር ይገባል ብለዋል።

ከልማትና ከትብብር ውጪ ያለው አማራጭ የጥፋት መንገድ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ሁሉም አካላት ለክልሉና ለሀገር ዕድገት በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሸናፊ እንዳለ
#ethiopia #bahirdar #felegegion #resort #ebc

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.