የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀብት መጠን ወደ 2.87 ትሪሊዮን ብር አደገ
*********************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሀብት መጠን ወደ 2.87 ትሪሊዮን ብር ማደጉን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።
ባንኩ በ2025/26 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 54.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡንም አቶ አቤ ሳኖ የባንኩ የሦስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ በተገመገመበት ወቅት ተናግረዋል።
በዘጠኝ ወራት ከፍተኛ ገቢ መሰብሰቡን ያነሡት ፕሬዚዳንቱ፣ ባንኩ ከገቢው ጋር የሚመጣጠን የወጪ አጠቃቀም እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በስኬት ለማጠናቀቅ እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማስመዝገብ መላው የማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች በተቀናጀ መልኩ ከፍተኛ ርብርብ እንዲያደርጉም ጥሪ ማቅረባቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#ebc #ethiopia #cbe #capital

1 month ago