በጤና ተቋማት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ተግባራዊ የማድረግ ስራ መጀመሩ ተገለጸ
#ethiopia | የጤና ሚኒስቴር የዲጂታል ጤና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገመቺስ መልካሙ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ጋር ለማጣጣም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ የማዋል ስራ በስፋት እየተሰራ ይገኛል።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር በዋነኝነት የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማጠናከርና በጤና ተቋማት የሚሰጡ የህክምና ምርመራዎችን በቴክኖሎጂ የታገዙ ለማድረግ ያለመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመረጃ አያያዝን በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተመልክቷል።
በተለይም በጤና ኬላዎች ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የኤሌክትሮኒክ ኮሚዩኒቲ ሄልዝ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (eCHIS) እና የሄልዝ ፖስት አሲስታንት (Health Post Assistant) የተባሉ ሶፍትዌሮች የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ስራ እያቀለሉ ይገኛሉ።
እነዚህ ሶፍትዌሮች የጤና ባለሙያዎች የህብረተሰቡን የጤና መረጃ እንዲመዘግቡ ከማስቻላቸው ባለፈ በስራ ላይ ለሚገጥሟቸው ውስብስብ የህክምና ጥያቄዎች በጽሁፍና በድምጽ አማራጭ ፈጣን ምላሽና መረጃ እንዲያገኙ የሚያግዝ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የተቀናጀባቸው ናቸው።
እንደ ሀገር እስካሁን ባለው መረጃ የኤሌክትሮኒክ ኮሚዩኒቲ ሄልዝ ኢንፎርሜሽን ሲስተም የዲጂታል አሰራር በ9 ሺህ የጤና ኬላዎች ላይ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን በዚህም ከ31 ሚሊዮን በላይ የሚሆን የህዝብ ቁጥር በመረጃ ቋት ውስጥ ተካቶ አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጓል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የባለሙያዎችን አቅም የሚደግፈው የ ሰው ሰራሽ አስተውሎ ቴክኖሎጂ በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ በሙከራ ደረጃ እየተተገበረ ሲሆን የሙከራ ሂደቱ ውጤታማነት እየታየ ወደ ቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች በስፋት ለማድረስ እቅድ ተይዟል።
ይህ ቴክኖሎጂ በተለይ ራቅ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እውቀታቸውን በየጊዜው እንዲያዳብሩ፣ ስለ አዳዲስ በሽታዎችና መድሃኒቶች ፈጣን መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን መሪ ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል።
በቀጣይም የቴክኖሎጂው ተጠቃሚነት በገጠር ብቻ ሳይወሰን በከተማም ደረጃ ሰፊ ተደራሽነት እንዲኖረው ሚኒስቴሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
📷 ሳውራ

4 months ago