አዋሽ ባንክ ለፋሲካ በዓል ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ድጋፍ አደረገ
#fastmereja I አዋሽ ባንክ የ2018 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ “ክብራችን ወገናችን - ደስታችን ማካፈላችን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ለሚገኙ ከ5 ሺህ በላይ አረጋውያንና አቅመ ደካማ ወገኖች የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ባንኩ ዛሬ በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒዓለም ካቴድራል የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሂዷል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተመረጡ ለእነዚሁ ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 5 ሊትር ዘይት፣ 25 ኪሎ ዱቄት እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።
ባንኩ ለማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን፣ ባለፈው የ2024/25 የሒሳብ ዓመት ብቻ ለማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባራት ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጿል። ይህም በትምህርት፣ በጤና፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአቅመ ደካሞችን ቤት በመገንባት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተጠቅሷል።
ባንኩ ካለፉት 31 ዓመታት ጀምሮ እንዲህ ያሉ ሰው-ተኮር ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሶ፣ ወደፊትም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
በተጨማሪም አዋሽ ባንክ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ1005 በላይ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን፣ ከ16 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

4 months ago