Logo
Getu Temesgen
“መሸነፍ አይገባንም ነበር” - ሚኬል አርቴታ
#ethiopia | ቡድናቸው በኤፌ ካፕ (FA Cup) ከሳውዝሀምፕተን ጋር በነበረው ጨዋታ የደረሰበት ሽንፈት የሚገባው እንዳልነበር በቁጭት ገለጹ።

አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ ጨዋታውን ለሁለት ጊዜያት ደግመው መመልከታቸውንና ቡድኑ በሜዳ ላይ ካሳየው እንቅስቃሴ አንፃር ሽንፈት የማይገባው እንደነበር አፅንዖት ሰጥተዋል።

አርቴታ አክለውም “ይህ እግርኳስ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ከእኛ ማንነት ጋር በተያያዙ ስህተቶች እንቀጣለን” በማለት፣ ምንም እንኳን ውጤቱ ባይሳካም ሽንፈቱ ከጨዋታው ይዘት ይልቅ በትንንሽ ስህተቶች የመጣ መሆኑን አመልክተዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvah #አርሰናል #ሚኬልአርቴታ #ኤፌካፕ #እግርኳስ #የስፖርትዜና #ሳውዝሀምፕተን #arsenal #arteta #facup #footballnews

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.