Logo
Getu Temesgen
የዓለም የሙዚቃ ንግሥት ሴሊን ዲዮን ወደ መድረክ ልትመለስ ነው!
#ethiopia | ካናዳዊቷ የሙዚቃ ኮከብ ሴሊን ዲዮን፣ ላለፉት ስድስት ዓመታት ከቆየችበት የጤና እክል አገግማ በመጪው መስከረም ወር ወደ መድረክ እንደምትመለስ በይፋ አስታወቀች።

ድምፃዊቷ "Stiff-Person Syndrome" በሚባለውና የጡንቻ መሸማቀቅን በሚያስከትል ብርቱ የጤና ችግር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከሙዚቃው ዓለም ርቃ የቆየች ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጋት ከፍተኛ ብርታትና ተነሳሽነት ላይ እንደምትገኝ ገልጻለች።

ሴሊን ዲዮን ዳግም ወደ አድናቂዎቿ የምትመለስበትን ተከታታይ ኮንሰርቶች በፈረንሳይ ፓሪስ ለማቅረብ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ስትገልጽ፣ በሕመም ወቅት አድናቂዎቿ ላሳዩዋት የማይረሳ ፍቅርና ድጋፍ ምስጋናዋን አቅርባለች።

የ56 ዓመቷ አርቲስት በቅርቡ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ መክፈቻ ላይ በኤፌል ታወር ስር ተገኝታ ባቀረበችው ድንቅ ብቃት፣ ወደ መድረክ ለመመለስ ያላትን ጥንካሬ ማሳየቷ የሚታወስ ነው።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #አራዳfm #celinedion #musicnews #celinedionreturns #parisconcerts #legend #musicstar #entertainmentnews

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.