Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ የቢሊዮን ዶላር "ድብቅ" ሚሳኤሎችን ማንቀሳቀስ ጀመረች
#ethiopia | ​ብሉምበርግ (Bloomberg) ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ አሜሪካ እጅግ ዘመናዊና ረጅም ርቀት ተጓዥ የሆኑትን JASSM-ER ክሩዝ ሚሳኤሎች በኢራን ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ እያከማቸች ትገኛለች።
​
እያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ዶላር የሚገመቱት እነዚህ ሚሳኤሎች፣ የጠላትን የራዳር መከላከያ ሰብረው በመግባት ኢላማን በከፍተኛ ጥንቃቄ የመምታት "ድብቅ" (Stealth) ብቃት አላቸው።

​ሚሳኤሎቹ ከፓስፊክ ውቅያኖስ፣ ከመካከለኛው አሜሪካና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተሰብስበው ወደ አሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) እና በእንግሊዝ ወደሚገኘው የፌርፎርድ የአየር ኃይል ጣቢያ እየተጓጓዙ ነው።

​ ይህ ግዙፍ ክምችት በአንድ አካባቢ መሰብሰቡ፣ በኢራን ላይ ሊሰነዘር ለሚችል መጠነ ሰፊና "የማያዳግም" ጥቃት እንደ ቅድመ ዝግጅት እየታየ ነው።
​
ትዕዛዙ የተሰጠው በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ሲሆን፣ ይህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጦራቸውን እንደሚያወጡ ከገለጹበት ንግግር በተቃራኒ ወታደራዊ ዝግጁነቱ እየጠነከረ መሄዱን ያሳያል።

​#getu #usmilitary #jassmer #irantension #bloombergreport #missiledefense #globalsecurity #middleeastcrisis #trumpadmin #stealthmissiles #አሜሪካ #ኢራን #ሚሳኤል #ጦርነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.