“ተንበርክከው የትዳር ጥያቄ የሚያቀርቡ ወንዶች ይታሰሩ!” - የኡጋንዳው ጄኔራል
#ethiopia | የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ እና የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ባስተላለፉት አዲስ መልዕክት አለም አቀፍ መነጋገሪያ ሆነዋል። ጄኔራሉ ወንዶች ለፍቅረኞቻቸው የጋብቻ ጥያቄ ለማቅረብ መንበርከካቸውን ክፉኛ በመንቀፍ፣ ድርጊቱን የሚፈጽሙ ወንዶች በህግ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ይገባል ብለዋል።
በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ይህንን ድርጊት “የምዕራባውያን ባህል ተጽዕኖ” እና “የወንድ ልጅን ክብር የሚያሳንስ” ሲሉ አጣጥለውታል።
ይህ መግለጫቸው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ ክርክር የፈጠረ ሲሆን፤ አንዳንዶች ሀሳቡን የአፍሪካን ባህላዊ እሴቶች የመጠበቅ እና የማስከበር እርምጃ ነው በማለት ሲደግፉት፣ ሌሎች ደግሞ በግለሰቦች ነጻነት ውስጥ ጣልቃ መግባት ነው ሲሉ አጥብቀው ተቃውመውታል።
ይሁን እንጂ የጄኔራሉ ንግግር ከእሳቸው የተለመዱ አወዛጋቢ የግል አስተያየቶች አንዱ እንጂ፣ በኡጋንዳ ተንበርክኮ ጥያቄ ማቅረብን የሚከለክል ምንም አይነት ይፋዊ ህግ ወይም ፖሊሲ የለም።
ባለስልጣናትም በመንግስት በኩል የተለወጠ አቋም አለመኖሩን ያረጋገጡ ሲሆን፣ እስካሁንም በዚህ ጉዳይ ምክንያት የተያዘ ወይም የታሰረ አንድም ሰው አለመኖሩ ታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ዜና #ኡጋንዳ #አፍሪካ #ባህል #ሙሁዚካይኔሩጋባ #uganda #news #africa

4 months ago