የውጭ ምንዛሬን የሚታደገው የዳታ ማከማቻ አገልግሎት በኢትዮጵያ ተጀመረ!
#fastmereja I በምሥራቅ አፍሪካ የዳታ ማዕከል አገልግሎት ፈር ቀዳጅ የሆነው ዊንጉ አፍሪካ፣ ተቋማት የመረጃ ደህንነታቸውን በሀገር ውስጥ እንዲጠብቁ የሚያስችል ዘመናዊ መድረክ በዛሬው ዕለት በይፋ አስተዋወቀ።
ይህ አዲሱ የክላውድ መድረክ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የመንግሥትና የግል ተቋማት መረጃዎቻቸውን በሀገር ውስጥ እንዲያከማቹና የሀገሪቱን የዳታ ደህንነት ሕግጋት እንዲያከብሩ ዕድል የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
በተለይም በባንክ፣ በኢንሹራንስና በሌሎች ከፍተኛ መረጃ በሚይዙ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች አስተማማኝ መሠረተ ልማት እንደሚሆን ታምኖበታል።
የዊንጉ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና መስራች ዴሞስ ኪሪያኩ በምረቃው ወቅት እንደገለጹት፣ለአፍሪካ ቢዝነሶች ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ መድረክ መሆኑን ገልፀዉ"ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ሕግን ያከበረና እንደ ቢዝነሱ ዕድገት ሊሰፋ የሚችል የክላዉድ አገልግሎት እያቀረብን ነው' ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
ይህ አገልግሎት ከተለመዱት ዓለም አቀፍ የክላውድ አገልግሎቶች የሚለየዉ፣ተቋማት ለአገልግሎቱ ክፍያ የሚፈጽሙት በሀገር ውስጥ ገንዘብ (በብር) በመሆኑ የውጭ ምንዛሬ እጥረትንና መለዋወጥን ማስቀረቱ፣መረጃዎች የሚቀመጡት በሀገር ውስጥ ባሉ የዳታ ማዕከላት በመሆኑ ተቋማት መረጃዎችን በከፍተኛ ፍጥነትና ያለምንም መቆራረጥ እንዲያገኙ እንደሚያስችል በመድረኩ ተገልጿል።
በተጨማሪም መድረኩ እንደ Azure እና AWS ካሉ ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ጋር ተቀናጅቶ መሥራት የሚችል በመሆኑ፣ ድርጅቶች እንደ ፍላጎታቸው አገልግሎቱን እንዲመርጡ ዕድል እንደሚሰጥ ተጠቅሷል።
ዊንጉ አፍሪካ በዘርፉ ያለውን የረጅም ጊዜ ልምድ በመጠቀም “ዊንጉ ኮምፒውት"፣ "ዊንጉ ድራይቭ" እና "ዊንጉ ሴኪውሪቲ" የተሰኙ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረቡንም በዚህ መድረክ ገልጿል።
ይህ ጅምር የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከማጠናከሩ ባለፈ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በዝቅተኛ ወጪ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀሙ መንገድ የሚከፍት መሆኑ ተጠቁሟል።

4 months ago