Logo
Getu Temesgen
ሩሲያ ለሽያጭ ቤንዚን ወደ ውጭ ሀገራት አልክም አለች
#ethiopia | የሩሲያ መንግስት ከፊታችን መጋቢት 23 ቀን 2018 ጀምሮ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቆይ የቤንዚን ኤክስፖርት እገዳ ለመጣል መወሰኑን አስታወቀ። ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ ተከትሎ የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ የኢነርጂ ሚኒስቴር እገዳውን የሚጥል ረቂቅ ደንብ እንዲያዘጋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። እንደ መንግስታዊው የዜና ወኪል ታስ (TASS) ዘገባ ከሆነ፣ እገዳው እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

ሩሲያ ይህን ጠንከር ያለ እርምጃ እንድትወስድ ካስገደዷት ምክንያቶች መካከል፦

* በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ሳቢያ የሚታየውን የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ መቋቋም፣
* የሀገር ውስጥ የነዳጅ አቅርቦትን ማረጋጋት፣
* በሀገር ውስጥ የሚታየውን የዋጋ ንረት መቆጣጠር ዋነኞቹ ናቸው።

ሩሲያ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ ወደ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ ቤንዚን ለዓለም ገበያ ያቀረበች ግዙፍ ሀገር በመሆኗ፣ አሁን የጣለችው እገዳ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

በተለይም የነዳጅ ፍላጎት በሚጨምርባቸው ወቅቶች ላይ አቅርቦቱ መቋረጡ የዋጋ ጭማሪን ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተሰግቷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #russia #fuelexportban #globalenergy #oilmarket #gasolineprices #economynews #alexandernovak #tass #etbusinessview #ቅዳሜገበያ

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.