Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር በዓለም አቀፍ መድረክ! 🇪🇹🇰🇷
#ethiopia | ​በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የባህል እና የኪነጥበብ ሙያተኞች ህብረት ዋና መስሪያ ቤት፣ ኢትዮጵያዊውን አቶ ገብረማርያም ይርጋን የምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾመ።

​አቶ ገብረማርያም በአሁኑ ወቅት የአማራ ባህል፣ ኪነጥበብና ዝክረታሪክ ም/ኃላፊ ሲሆኑ፣ በባህል ዲፕሎማሲው ዘርፍ ባላቸው ንቁ ተሳትፎ ይታወቃሉ።

ይህ ሹመት የኢትዮጵያንና የአፍሪካን ጥበብ ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ለማውጣት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ታምኖበታል።

​አቶ ገብረማርያም ስለ ሹመቱ ሲናገሩ፦ "ይህን ሹመት እንደ ክብር ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ስትራቴጂክ አደራ እቀበላለሁ" ብለዋል።

​ለአቶ ገብረማርያም ይርጋ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን! 👏✨
#ኢትዮጵያ #ባህል #ኪነጥበብ #ደቡብኮሪያ #ሹመት #ጌቱተመስገን #ባህልዲፕሎማሲ #ethiopia #culture #art #globalleadership #southkorea #culturaldiplomacy

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.