"እስራኤል ሽንፈት ካጋጠማት ከጎኗ እንቆማለን" የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ
#ethiopia | የኡጋንዳ መከላከያ ሠራዊት አዛዥ እና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ የሆኑት ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭት ሀገራቸው ከእስራኤል ጎን እንደምትሰለፍ በይፋ ገለጹ።
ጄኔራሉ በኤክስ (X) ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዓለም በጦርነት ቢሰለችም እስራኤልን "ስለማጥፋት ወይም ስለማሸነፍ" የሚነገሩ ወሬዎች ኡጋንዳን ወደ ጦርነቱ እንደሚያስገቧትና ከእስራኤል ጎን እንደምትቆም አስታውቀዋል።
ይህ አስተያየት የተሰነዘረው በኢራን እና በእስራኤል መካከል የሚደረጉ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃቶች እንዲሁም የቀጥታ ግጭቶች በከፍተኛ ሁኔታ በጨመሩበት ወቅት ነው።
ካይኔሩጋባ በቅርቡ በ1976 የኢንቴቤ ታጋቾችን ለማስለቀቅ በተደረገው ዘመቻ ለተገደለው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ወንድም—ዮናታን (ዮኒ) ኔታንያሁ—መታሰቢያ ሐውልት ለማቆም ማቀዳቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ ጠንከር ያሉና አወዛጋቢ አስተያየቶችን በመስጠት የሚታወቁ ሲሆን፣ አሁንም ይሄንኑ ንግግራቸውን ካሰራጩ በኋላ መልዕክቱን ወዲያውኑ መልሰው ማጥፋታቸው ተስተውሏል።
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ እያየለ መምጣቱ ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #uganda #israel #middleeastconflict #muhoozikainerugaba #geopolitics #newsupdate #ethiopia

4 months ago