"ማዱሮ በኒውዮርክ ፍርድ ቤት፦ 'እኔ የሀገሬ ህገ-መንግስታዊ ፕሬዝዳንት ነኝ!'"
የቀድሞው የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው ሲሊያ ፍሎሬስ በኒውዮርክ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ማዱሮ በዕፅ ዝውውር የተመሰረተባቸውን ክስ በፅኑ የተቃወሙ ሲሆን፣ ጠበቃቸው ባሪ ፖላክ የአሜሪካ መንግስት ለመከላከያ ወጪ የሚሆን የቬንዙዌላን ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ በማገዱ "ህገ-መንግስታዊ መብታቸው ተጥሷል" ሲሉ ተከራክረዋል።
ባለፈው ጥር ወር በካራካስ በቁጥጥር ስር የዋሉት ማዱሮ፣ ለፍርድ ቤቱ "ንፁህ ነኝ፣ እኔ የሀገሬ ህገ-መንግስታዊ ፕሬዝዳንት ነኝ" በማለት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
አሜሪካ ከቬንዙዌላ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ብታድስም፣ ማዱሮ ግን በብሩክሊን ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ። ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ የዕድሜ ልክ እስራት ሊፈረድባቸው ይችላል።
ምንጭ፦ Associated Press

4 months ago