በኢትዮጵያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን የሚያከብረው "ሀደ ሲንቄ" አዋርድ በ2026 ሊካሄድ ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ የተለያዩ ዘርፎች ጉልህ አሻራ ያረፉ እና ለውጥ ያመጡ ሴቶችን እውቅና ለመስጠት ያለመው "ሀደ ሲንቄ" አዋርድ በዚህ ዓመት እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የአዋርዱ መስራች እና ሰብሳቢ ገሊላ በኩማ እንደገለጹት፣ ሽልማቱ የሴቶችን ድምፅ ለማሰማት እና በሀገር ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና ለማጉላት ያለመ ነው ብለዋል።
"ሀዳ ሲንቄ" ምንድን ነው?
"ሀደ ሲንቄ" የሚለው ስያሜ ትርጉም ተጽዕኖ ፈጣሪ፣ ድምፃቸው የሚሰማ፣ ለፍትህና ለሰላም የሚቆሙ እንዲሁም የሴቶችን መብት የሚያስከብሩ ሴቶችን የሚገልጽ ነው።
"ሲንቄ" በባህላዊ እሴት ውስጥ የስልጣን እና የሰላም ምልክት ተደርጎ የሚወሰድ ቅዱስ በትር ሲሆን፣ ሴቶች ይህንን በመያዝ ጦርነትን የማስቆም እና ሰላምን የማውረድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።
የ''ሀደ ሲንቄ አዋርድ'' ዓላማ በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መልካም ተጽዕኖ የፈጠሩ፣ የተማሩ፣ የሰሩ እና በሀገሪቱ ላይ የራሳቸውን አሻራ ያሳረፉ ሴቶችን እውቅና መስጠት ነው መሆኑ ተገልጿል።
ሽልማቱ ሁሉንም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚያካትት ሲሆን፣ በማንኛውም መስክ ውጤታማ የሆኑ ሴቶችን የሚመለከት ይሆናል።
የሽልማት ስነ-ስርዓቱ የሚከናወንበት ዝርዝር ቀን እና ቦታ ወደፊት በመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የሀደ ሲንቄ አዋርድ የሴቶችን የአመራርነት እና የማህበራዊ ተሳትፎ ሚና ከማሳደግ ባለፈ፣ የጥንቱን የሴቶች የሰላም እና የፍትህ እሴት ወደ ዘመናዊው አውድ ለማምጣት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#womenawards2026 #ethiopianwomen #empowerment #peaceandjustice #sinkeauthority #addisababa #ethiopia

4 months ago