በኮሪደር ልማት ስም ከሚነግዱና ደንበኞችን ከሚያጭበረብረው "የየአብ መስታወት ስራ" (Yeab Glass) ራሳችሁን ጠብቁ!
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ምክንያት በርካታ ነዋሪዎችና የንግድ ተቋማት የህንፃዎቻቸውን የፊት ለፊት ገጽታ በመስታወት ስራ እያዘመኑ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ደንበኞችን የሚያጭበረብሩና የመንግስትን ታክስ የሚሰውሩ ድርጅቶች መበራከታቸው አሳሳቢ ሆኗል።
በቦሌ ቡልቡላ ስታዲየም ፊት ለፊት የሚገኘው "የየአብ መስታወት ስራ" (Yeab Glass) የተባለው ድርጅት በደንበኞች ላይ እያደረሰ ያለው በደል ለዚህ ማሳያ ነው።
የተፈጸሙ ዋና ዋና ጥሰቶች፦
* የገንዘብ ማጭበርበር፦ ለህንፃ በር መስታወት ስራ 110,000 (አንድ መቶ አስር ሺህ) ብር ሙሉ ክፍያ ተቀብሎ፣ በ15 ቀን ውስጥ አጠናቅቃለሁ ብሎ የተስማማውን ስራ ከ2 ወር በላይ አጓትቷል።
* ጥራት የጎደለው ስራ፦ ከብዙ እንግልት በኋላ ተገጥሞ ያለቀው ስራ የተሰበረ መስታወት ሲሆን፣ እስካሁንም ለበሩ ቁልፍ ሳይገጥም ደንበኛውን ለከፍተኛ ስጋትና እንግልት ዳርጓል።
* የታክስ ስወራ፦ ለተከፈለው 110 ሺህ ብር ህጋዊ የቫት (VAT) ደረሰኝ ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆን የመንግስትን ታክስ እየሰወረ ይገኛል።
🔥ለገቢዎች ቢሮ የቀረበ ጥቆማ፦
ይህ ድርጅት ደረሰኝ ባለመቁረጥ የሚፈጽመውን የታክስ ስወራ የሚመለከተው የገቢዎች ባለስልጣን ጥብቅ ክትትል እንዲያደርግበት እናሳስባለን። ለክፍያው ማስረጃ የሚሆን የባንክ የክፍያ ስሊፕ (Bank Slip) በእጃችን የሚገኝ በመሆኑ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን።
ማሳሰቢያ፦
ህዝባችን በዚህ ድርጅት እንዳይታለልና ገንዘቡን ለከንቱ ብክነት እንዳይዳርግ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። "የየአብ መስታወት ስራ" (Yeab Glass) ላይ የሚሰሩ ሰራተኞችና ባለቤቶች ደንበኛን ማክበርና የገቡትን ቃል መፈጸም ሲገባቸው አሳሳች ስራ እየሰሩ በመሆኑ ህዝብ ሊያውቃቸው ይገባል።

3 months ago