Logo
YenetaTube
በአዲስ አበባ የተካሄደው 1ሺ447ኛው የኢድ አልፈጥር የሶላት ስነ-ስርዓት በድምቀት መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ሌሎች የእምነቱ አባቶች፣ የውጭ ሃገር አምባሳደሮች እና የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲሁም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየምና በዙሪያው በሚገኙ ጎዳናዎች የተካሄደው የኢድ አልፈጥር ረመዳን የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የሶላት ስነ-ስርአቱ በስኬት እንዲጠናቅ የጸጥታ አካላት እቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መግባታቸውን ጠቅላይ መምሪያው አስታውሶ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በጋራ በመሰራቱ ስኬታማ የኢድ ሶላት ማከናወን እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የኢድ ሶላት በስኬት እንዲከበር የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጋቸውን ፖሊስ አስታውቆ ለዚህም ምስጋናው አቅርቧል፡፡

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በዓሉ የሠላም የደስታ እንዲሆንላቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በፀጥታ ተቋማት ስም በድጋሚ መልካም ምኞቱን ገልጾ የከተማውን ሠላምና ደህንነት ለማስከበር በሚከናወኑ ልዩ ልዩ ተግባራት ላይ ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል።

Addis Ababa police

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.