Logo
SeledaPost
ሰላም ከራስ ይጀምራል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዒድ መልዕክታቸው ለሀገራዊ መግባባት ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለ1447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሰላም ከራስና ከፈጣሪ ጋር ካለ ጤናማ ግንኙነት እንደሚመነጭ በመግለፅ ረመዳን የሰው ልጅ ኅሊናውን የሚሰበስብበትና ራሱን የሚገራበት ወር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ውስጣዊ ሰላም የሌላቸው አካላት የማኅበረሰቡን ደህንነት እንዲያናጉ ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲሉ መልዕክታቸው ላይ ፅፈዋል።

የኢትዮጵያው መሪ ​ የግንቦት ወር ምርጫ ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ድል የምትቀዳጅበት በር ነው ያሉ ሲሆን ዜጎች በስክነትና በጨዋታው ሕግ በመመራት የታሪካዊ ሂደቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ግጭትን፣ መግደልንና ማፈናቀልን የኋላ ቀርነት መገለጫዎች ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ብልጽግና የሚረጋገጠው ዜጎች ለማኅበረሰቡ ሰላምና እድገት ሲጨነቁ ነው ብለዋል።

ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች "ዒድ ሙባረክ" በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

seledadotio
seledadotio
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.