ኢድ ሐሙስ ወይንስ ዓርብ?
የሳዑዲ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መግለጫ ሰጠ።
መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም (ሪያድ)
የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመላው ግዛት የሚገኙ ሙስሊሞች የሸዋልን ወር (የኢድ አልፈጥር) ጨረቃ ረቡዕ ምሽት መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም (March 18) እንዲጠባበቁ ጥሪ አቀረበ።
እንደ ኡሙል ቁራ የቀን አቆጣጠር፣ ረቡዕ መጋቢት 9 የረመዳን ወር 29ኛው ቀን ሲሆን፣ በዕለቱ ጀንበር ስትጠልቅ የጨረቃ እይታ ይከናወናል።
1. ረቡዕ ምሽት ጨረቃ ከታየች፦
ሐሙስ መጋቢት 10 (March 19) የዒድ አልፈጥር የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።
2. ጨረቃ ካልታየች፦
የረመዳን ወር 30 ቀናት ተሞልቶ ኢድ ዓርብ መጋቢት 11 ይውላል።
* በማንኛውም የአገሪቱ ክፍል ጨረቃን በዓይን ወይም በቢኖክዩለር የተመለከተ ግለሰብ በአቅራቢያው በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርቦ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ አሳስቧል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይፋዊ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የምስክሮችን ቃል በጥብቅ እንደሚያጣራ ገልጿል።
ለዚሁ ተግባር በተመረጡ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የጨረቃ ክትትል ኮሚቴዎች ረቡዕ ምሽት ዝግጅታቸውን አጠናቀው እንደሚጠባበቁ ታውቋል።
ከወዲሁ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
Via GN
seledadotio

5 months ago