የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወለደ ሰማዕት) ክቡር አስከሬን ሽኝትን በተመለከተ የተዘጋጀ መርሐ ግብር
"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።" ማቴ 28፡19
“የአገልጋይን ሰው ሞት ቸል አትበል ምርር ብለህ አልቅስለት አጽናንተው አዝንለት እንደ ሀገሩ ልማድ አልቅስለት ስለ ሀገሩ ልማድ አንድ ቀን ሁለት ቀን አልቅስለት የብስጭት ሀይል የሚያደክም ስለሆነ ስለ ብስጭት ሀዘን እንዳይገባህ ከዚህ በኋላ ልቅሶህን ተው።” መጽሐፈ ሲራክ 38 16-18
መርሐ ግብር:-
* እሁድ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም (March 8, 2026) በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል።
1. እሁድ ከቅዳሴ በኋላ በርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጽረ ግቢ በላይኛው መኪና ማቆሚያ የአካባቢው አድባራት እና ገዳማት አገልጋዮች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሰብስበው ሀዘናቸውን ይገልጻሉ።
2. ሰኞ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም (March 9, 2026) ከቀኑ 12pm - 4pm ሰዓት ጀምሮ በላይኛው ትራቨለር ለቅሶ መድረስ ለሚፈልጉ ሁሉ ቦታው ክፍት ይሆናል።
4. ሰኞ ከቀኑ 4:30pm - 7:30pm የአካባቢው አድባራት እና ገዳማት አገልጋዮች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሰብስበው በሠርክ ጸሎት እና በትምህርተ ወንጌል፣ በውዳሴ ማርያም ሥነ ሥርዓት ሲዘክሩ ያመሻሉ።
5. ሰኞ ከምሽቱ 7 ሰዓት ክቡር አስከሬኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይገባል።
6. ከሌሊቱ 1am የአካባቢው አድባራት እና ገዳማት አገልጋዮች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሰብስበው በሰዓታት ቆመው ያድራሉ።
7. ማክሰኞ ከጠዋቱ 9am - 12pm የአካባቢው አድባራት እና ገዳማት አገልጋዮች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሰብስበው ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል።
8. ማክሰኞ 12pm የመምህር ዘላለም ወንድሙ የሕይወት ታሪክ እና የወዳጅ ዘመድ ምስክርነት ይሰጣል።
9. ማክሰኞ በፓትርያርኩ አጭር ትምህርተ ወንጌል ይሰጣል።
10. ማክሰኞ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ተሰጥቶ ክቡር አስከሬኑ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ሽኝት ከተደረገ በኋላ ለመታሰቢያ የተዘጋጀው ጸበል ጻዲቅ ተቀምጦ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ይሆናል። የመምህራችን የወለደ ሰማዕትን ነፍስ ከቅዱሳን ጋር ይደምርልን።
ማሳሰቢያ፦ ካህናት እና አገልጋዮች እንዲሁም ምእመናን በሙሉ ነጭ ልብስ ለብሳችሁ እንድትገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
አድራሻ፡ 1350 Buchanan St. NW, Washington, D.C 20011
ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

3 months ago