ከህግ በላይ ማንም የለም! የዩኒፎርም ክብርና የዜጎች ደህንነት
ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ምስል/ቪዲዮ እጅግ ልብ የሚሰብርና የሚሰቀጥጥ ነው አንድ የአይሱዙ ሹፌር "ደርቦ ነድተሃል/ገልብጠኸኝ ነበር " በሚል ሰበብ በመከላከያ ሰራዊት አባል በክላሽንኮቭ ተገዶ ተንበርክኮ ሲደበደብ ማየት ማንንም ሰብአዊ ፍጡር ያሳዝናል።
የትራፊክ ጥፋትም ሆነ አደጋ ቢከሰት ውሳኔ መስጠት ያለበት የትራፊክ ፖሊስና የፍትህ አካላት እንጂ በግል መሳሪያን አውጥቶ መቅጣት አይደለም ዩኒፎርም የህግ ማስከበሪያ እንጂ የጭቆና መገልገያ መሆን የለበትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የህዝብ አለኝታና የሀገር ጋሻ ነው።
እንዲህ ያሉ ጥቂት ግለሰቦች የሚፈጽሙት የዲሲፕሊን ጉድለትና የግል በቀል ደምና አጥንቱን እየገበረ ያለውን መላውን የሰራዊቱን ስም ያጎድፋል።
ማንኛውም ዜጋ ጥፋተኛ እንኳን ቢሆን ሰብአዊ ክብሩ ተጠብቆ በህግ ፊት የመቅረብ መብት አለው።
አንድን ሹፌር አንበርክኮ መደብደብ የለየለት ወንጀልና ስርዓት አልበኝነት ነው።
የሚመለከተው የመከላከያ ከፍተኛ አመራርና የፍትህ አካላት ይህንን ድርጊት የፈጸመውን ግለሰብ ህግ ፊት ማቅረብ አለባቸው
ሰራዊቱ የህዝብ ወገንተኝነቱን በተግባር እንዲያሳይ እንዲህ ያሉ በስሜት የሚነዱ አባላትንም ከቅዱስ ሙያው እንዲያርቅ ይመከራል
ፍትህ ለተበዳዩ ሹፌር!
ክብር ለህግ የበላይነት! #ethiopia #humanrights #accountability #ethiopiandefenseforce #justice

5 months ago