“ለምን ስራቸው ወጣ ብለህ የቅናት መንፈስ ውስጥህ አይግባ” ኤምሲ ሲያምረኝ ለሳሚ ዳን ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጠ!
#fastmereja I በቅርቡ በድምጻዊ ሳሚ ዳን በኢትዮጵያን ራፐሮች መካከል ስላለው ዲስ አስተያየት ሰጥቶ ነበር የመጀመሪያው መልስ ሰጪ ራፐሩ ኤምሲ (MC) ሲያምረኝ ሆኗል።
ሳሚ ዳን በሰጠው አስተያየት ላይ "ስድብ" በሚል ለገለጸው ነጥብ፣ ሲያምረኝ የሂፕ ሆፕን ታሪክና ባህል በመጥቀስ ምላሹን ሰጥቷል።
ሲያምረኝ ሂፕ ሆፕ በ70ዎቹ በኒው ዮርክ ሲመሰረት "ባትል ራፕ" የቃላት ጦርነትና ታለንትን ማሳያ እንጂ የግል ጥላቻ እንዳልሆነ አስረድቷል። "ይህ ጌም ነው፤ በቅናት መንፈስ ሊታይ አይገባም" ሲልም አክሏል።
አዲስ በለቀቀው የዲስ ትራክ ላይ "ግጥሙን ሳሚ ዳን ነው የጻፈለህ?" ለሚሉ የኮሜንት አስተያየቶች፣ ግጥሙን ራሱ እንደጻፈውና የራሱ የፈጠራ ውጤት መሆኑን በኩራት ገልጿል።
ሲያምረኝ ሳሚ ዳን ሰዎችን "በመላስ" እና "ጠቅ ጠቅ በማድረግ" እንደሚታወቅ በመጥቀስ፣ "የሙዚቃ ክብርህንና እድሜህን ወደ ጎን አድርገህ ሰዎችን ትልሳለህ" ሲል ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝሯል።
"ሌላውን ከመተቸትህ በፊት ራስህን እይ፣ ለምን ስራቸው ወጣ ብለህ የቅናት መንፈስ ውስጥህ አይግባ" የሚል መልዕክትም አስተላልፏል።
ሳሚ ዳን የሬጌ አርቲስት መሆኑን በማስታወስ፣ "ሬጌ ሰላምን፣ አንድነትንና ፍቅርን (Peace, Unity & Love) ይሰብካል እንጂ ስድብ የለበትም፤ የትኛው የሬጌ መርህ ነው ስድብን የሚፈቅደው?" ሲል ጠይቋል።
#showbiz

5 months ago