ከሪያዱ የድሮን ጥቃት በኋላ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ቤተሰቦች በግል አውሮፕላን ወደ ማድሪድ በረሩ የሚሉ ዘገባዎች እየተሰሙ ነው
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ የተሰነዘረውን የድሮን ጥቃት ተከትሎ፣ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ደህንነት የዓለም እግር ኳስ መነጋገሪያ ሆኗል።
በዓመት ከ200 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የሚከፈለው ሮናልዶ፣ በጸጥታ ስጋት ምክንያት ባለቤቱ ጆርጂና ሮድሪጌዝን እና አምስት ልጆቹን በ70 ሚሊዮን ዩሮ በሚገመት የግል አውሮፕላን ወደ ስፔን ማድሪድ መላኩ በሰፊው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ነው።
አል ናስር ከአል ዋስል ጋር ሊያደርገው የነበረው የኤዢያ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል።
ይሁን እንጂ ታዋቂው ጣልያናዊ ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ ሮናልዶ አገር ጥሎ ወጥቷል የሚለውን ወሬ አስተባብሏል።
እንደ ሮማኖ ገለጻ፣ ሮናልዶ በአሁኑ ወቅት በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በክለቡ አል ናስር የሕክምና ማዕከል ውስጥ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

3 months ago