Logo
YenetaTube
🚨 ሰበር ዜና፡ ስፔን የአሜሪካን የጦር አውሮፕላኖች አባረረች ጀርመን በምትኳ አጋርነቷን ለአሜሪካ አሳየች! 🇺🇸🇩🇪🇪🇸

በኢራን ላይ እየተሰነዘረ ያለውን ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ በኔቶ (NATO) አባላት መካከል ከፍተኛ ፍጥጫ ተፈጥሯል የዶናልድ ትራምፕ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ባወጣው መረጃ መሰረት ስፔን ለአሜሪካ ጦር ድጋፍ አንሰጥም በማለት በሮቿን ዘግታለች።

📌 በስፔን በኩል የተወሰደው እርምጃ፦

* ትራምፕ የሶሻሊስቱ የስፔን መንግስት በሮታ እና ሞሮን የሚገኙ የጋራ ወታደራዊ ካምፖች ለአሜሪካ የነዳጅ ቅብብል አገልግሎት እንዳይውሉ ከልክሏል ብሏል

* የመከላከያ ሚኒስትር ማርጋሪታ ሮብልስ "ምንም ዓይነት ድጋፍ አንሰጥም" በማለት በግልጽ ተናግረዋል።

* በዚህም ምክንያት ዘጠኝ (9) KC-135 Stratotanker የተባሉ የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች ከስፔን ግዛት እንዲወጡ ተደርገዋል።

ስፔን ጀርባዋን በሰጠችበት ወቅት ጀርመን አጋርነቷን አረጋግጣለች ሲል ትራምፕ አሳውቀዋል
እነዚህ አውሮፕላኖች በጀርመን የሚገኘው የራምስታይን (Ramstein) አየር ኃይል ካምፕ እንዲያርፉ ተፈቅዶላቸዋል ይህም አሜሪካ በኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የምታደርገው ጥቃት ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል አስችሏል።

ይህ ክስተት በኔቶ አጋሮች መካከል ያለውን ክፍፍል ያሳየ ሲሆን ስፔን በአሜሪካ የደህንነት ጥላ ስር እየኖረች ወሳኝ በሆነ ሰዓት አጋሯን መክዳቷ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ትችት እየቀረበባት ይገኛል። በሌላ በኩል ጀርመን ለአሜሪካ ያላትን የአጋርነት ቁርጠኝነት አሳይታለች ተብሏል።
#news #nato #usa #germany #spain #iran #military #breakingnews

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.