Logo
SeledaPost
#update

የፈተና ቀኖቹ ላይ ማስተካከያ ተደረገ።

አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ሙሉ ቀን በሚሰጡ የመውጫ ፈተናዎች ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።

አርብ ከቀኑ 5:00-7:30 ሰዓት የሚሰጠው ፈተና ከጁምዓ ሶላት ስግደት ጋር በተያያዘ እንዲሁም ቅዳሜ በሚሰጡ ፈተናዎች ላይ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በኩል ቅሬታዎች መቅረባቸውን ተከትሎ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማስተካከያ ማድረጉ ታውቋል።

በዚህም አርብ በሁለተኛ ክፍለ-ጊዜ (ከ5:00-7:30) ፈተናዎች ላይ ሽግሽግ የተደረገ ሲሆን፤ ቅዳሜ ፈተናው የማይሰጥ ይሆናል።

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተስተካከለውን መርሐግብር (ከላይ ተያይዟል) ለተፈታኝ  ተማሪዎቻቸው በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.