Logo
FIDEL POST NEWS
የ39 ዓመቱ የፍትህ ጉዞ በሞት ቅጣት ተቋጨ፡ በፍሎሪዳ ሌላኛው እስረኛ ተገደለ

​በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ለበርካታ አስርት ዓመታት በሞት ረድፍ ላይ የቆዩት የ65 ዓመቱ ሜልቪን ትሮተር ዛሬ በመርፌ በሚሰጥ መርዝ የሞት ቅጣት ተፈጸመባቸው።

​ ትሮተር እ.ኤ.አ. በ1986 በፓልሜቶ ከተማ የሱቅ ባለቤት የነበሩትን ቨርጂኒያ ላንግፎርድን በጭካኔ በማነቅና በቢላ በመውጋት በፈጸሙት ግድያ ጥፋተኛ ተብለዋል።

ሟች ከመሞታቸው በፊት የአጥቂውን ማንነትና የሥራ መታወቂያ መግለጻቸው፣ እንዲሁም በትሮተር ቤት የተገኘ የደም ነጠብጣብ ያለበት ቲሸርት ለቅጣቱ ዋነኛ ማስረጃ ሆነዋል።

​ ከ1987 ጀምሮ በተለያዩ የይግባኝ ሂደቶች ሲያልፉ የቆዩት ትሮተር፣ ጠበቆቻቸው "እድሜያቸው ለቅጣት አይመጥንም" በሚልና በሌሎች ምክንያቶች እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ የቅጣት ማቅለያ ቢጠይቁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል።

​ ይህ በፍሎሪዳ ግዛት የዘንድሮው ሁለተኛው የሞት ቅጣት ነው። የግዛቱ አስተዳዳሪ ሮን ዲሳንቲስ በ2025 ብቻ በ19 ሰዎች ላይ የሞት ቅጣት በማስፈጸም በግዛቱ ታሪክ ከፍተኛውን ቁጥር አስመዝግበዋል።

Sky News
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.