Logo
SeledaPost
ሲድሮ የተሰኘ ለቲክቶክ ቪዲዮ ጊፍት  መስጠት የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

ኢንፍራቴክ ሶፍትዌር ሰርቪስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ አፕሊኬሽን እና ሶፍትዌሮች እያበለጸገ ይገኛል። በዛሬው ዕለት   ለኢትዮጵያውያን የተሰራ "ሲድሮ" (Sydor) የተባለ አዲስ የሶሻል ሚዲያ አፕሊኬሽን እና የድርጅት ምስረታ ማካሄዱን  የተጽዕኖ ፈጣሪ እና የድርጅቱ ሼር ሆልደር የሆነው  አዶናይ ብርሃነ ለብስራት ሬዲዮ ተናግሯል።

​ይህ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያውያንን በራሳቸው ዲጂታል መድረክ ላይ በቀላሉ ለማገናኘት ታስቦ የተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ከማህበራዊ ሚዲያ አዝናኝነት አልፎ የራሱን የቴክኖሎጂ ድርጅት በመክፈት ትልቅ እርምጃ የወሰደው የዚህ ወጣት አዲስ አፕሊኬሽን፤ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቋል።

በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ከ7 እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርስ የቲክቶክ  ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን ጊፍቱ ኮይን በቴሌብር መግዛት  የሚቻል መሆኑ ተነግሯል

seledadotio
seledadotio
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.