Logo
Getu Temesgen
🏃‍♂️ አዲስ አበባ በስፖርት ልትደምቅ ነው! "ጎፈሬፊት ቱር" በይፋ ተበሰረ 🏃‍♀️
#ethiopia | ​ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠርና ስፖርትን የቤተሰብ ባህል ለማድረግ የሚያስችል ታላቅ የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ!

​የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ የፊት ኮርነር (Fit Corner) እና ታዋቂው የትጥቅ አምራች ጎፈሬ (Gofere) በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

​ይህ ስምምነት ምን ይዟል?

​🏆 እውቅና እና ማበረታቻ፦
በየአካባቢው ለሚገኙ የአካል ብቃት አሰልጣኞች እና የጤና ቡድኖች ተገቢውን እውቅና ይሰጣል።

​👕 የትጥቅ አቅርቦት፦
ጎፈሬ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ጥራት ያላቸውን የትጥቅ ምርቶች ለስፖርተኛው ተደራሽ ያደርጋል።

​📅 ቋሚ መርሐ ግብር፦
ስፖርቱ በየሳምንቱ ቅዳሜ በመደበኛነት እንዲከናወን ይደረጋል።

​ታላቅ የምስራች፦
የፊታችን የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም የሚጀምርና ለ6 ወራት የሚቆይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዘመቻ በይፋ ይጀመራል።

​"አካል ብቃትን በቤተሰብ ደረጃ ለማድረስና ስፖርትን ባህል ለማድረግ ሁላችንም እንሳተፍ!"

​#goferefittour #healthyethiopia #addisababasport #gofere #fitcorner #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.