የደብረጺዮን እና የጀነራል ታደሰ ዛቻ እና የጠሚ አብይ አህመድ ምላሽ።
የካቲት 11ን አስመልክቶ በትግራይ ክልል አመራሮች የተሰጡ መግለጫዎች እና የፌዴራል መንግሥት አቋም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ሰፊ ልዩነት አሳይተዋል።
የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል የድርጅቱን 51ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር፤ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ወልቃይት እና ራያ ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር ብለዋል። ዶ/ር ደብረፂዮን አክለውም የፌዴራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ተኩስ በመክፈት ስምምነቱን ጥሷል ሲሉ የከሰሱ ሲሆን፣ ጉዳዩ በሰላም የማይፈታ ከሆነ "የመመከት እና የመከላከል ግዴታ ውስጥ እንገባለን" የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ይሁን እንጂ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ የተጠቀሰው ነጥብ ከዶ/ር ደብረፂዮን ንግግር የተለየ ይዘት አለው። ስምምነቱ ወልቃይት እና ራያን ጨምሮ አወዛጋቢ አካባቢዎች (Contested Areas) መፍትሔ የሚያገኙት በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መሠረት እንደሆነ ይደነግጋል። በተጨማሪም ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ስምምነት ቢኖርም፣ አካባቢዎቹን በበላይነት የሚቆጣጠረውና ጸጥታውን የሚያስከብረው ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ የሆነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል።
በተመሳሳይ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በበኩላቸው፤ የፌዴራል መንግሥቱ የገባውን ቃል እንዲያከብርና ተፈናቃዮችን በመመለስ የትግራይን ሉዓላዊነት እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል። ጀነራል ታደሰ "ጦርነትን እንደ አማራጭ የሚመለከቱ ኃይሎች ካሉ በትግራይ በኩል ተገቢው መከላከል ይደረጋል" ሲሉ የጸጥታ ኃይላቸው የሕዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በተቃራኒው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳምንታት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ፤ ተፈናቃዮች ያልተመለሱት "ተፈናቃይን መያዣ (hostage) ያደረገ ፖለቲካ" በመኖሩ ነው ብለዋል። የፌዴራል መንግሥት አቋም ነዋሪዎች በሰላም እንዲኖሩና የአስተዳደር ጉዳዩን ራሳቸው እንዲወስኑት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "ማንኛውም ባለሥልጣን ከሚወስንላቸው ይልቅ ሕዝቡ በሰላም እየኖረ በየት በኩል መተዳደር እንዳለበት ራሱ መወሰን አለበት" በማለት ጉዳዩ በሕዝብ ውሳኔ መፈታት እንዳለበት አመልክተዋል።
seledadotio

4 months ago