ሶማሊላንድ በቱርክ ፕሬዝዳንት ንግግር ላይ ያላትን ቁጣ ገለጸች
ሀርጌሳ — የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ መንግስት የቱርክ ፕሬዝዳንት በቅርቡ ስለ ሶማሊላንድ የሰጡትን አስተያየት አጥብቃ እንደምትቃወም በዛሬው እለት ባወጣችው መግለጫ አስታወቀች።
ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም (February 18, 2026) ከሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ንግግር "ተቀባይነት የሌለው የውስጥ ጣልቃ ገብነት" ነው ሲል ገልጾታል።
በመግለጫው ላይ የተጠቀሱ ዋና ዋና ነጥቦች የቱርክ ፕሬዝዳንት ንግግር ሶማሊላንድ ከቀጣናዊ አጋሮቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማዳከም ያለመ ነው በማለት ሶማሊላንድ ኮንናለች።በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ሀገራት የውጭ ፖሊሲ ውሳኔዎች መወሰን ያለባቸው በራሳቸው በመንግስታቱ እና በህዝቦቻቸው መሆን እንዳለበት አሳስባለች።
የውጭ ሀገራት የርስ በርስ ሽኩቻ ወደ ቀጣናው መምጣት የለበትም ይህ መሆኑ የቀጣናውን መረጋጋት እና ትብብር አደጋ ላይ ይጥላል ስትል አስጠንቅቃለች።
ቱርክ ከቀጣናዊ ውጥረት ቀስቃሽ አቋሞች እንድትቆጠብ እና ለጋራ መከባበር ለጣልቃ-አልባነት እንዲሁም ለሉዓላዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች ተገዢ እንድትሆን ሶማሊላንድ ጥሪ አቅርባለች።
በመጨረሻም ሶማሊላንድ ከአጋሮቿ ጋር የምታደርገው ግንኙነት እና ዓለም አቀፍ እውቅናን ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ሰላማዊ ህጋዊ እና በህዝቦቿ ዲሞክራሲያዊ ምኞት ላይ የተመሰረተ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጣለች።
የኔታ ትዩብ

6 months ago