Logo
Getu Temesgen
ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስኬታማ መሆኑን ገለጸ
#ethiopia | የድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ባለፉት ጥቂት ወራት ባሳየው አስደናቂ እድገት፣ ከደንበኞች የሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ መሻገሩን አስታወቀ።

ተቋሙ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ይህ ስኬት በደንበኞች ዘንድ ያለውን ጠንካራ አመኔታ እና የጀመረው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውጤታማነት ማሳያ መሆኑን ገልጿል።

ድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ፣ ላለፉት ዓመታት ሲከተለው የነበረውን የተለመደ አሠራር በመቀየር፣ ከሁለት ዓመት ወዲህ ትኩረቱን በዲጂታል ፋይናንሲንግ ላይ ማድረጉ ተገልጿል። በተለይም ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በተከናወኑ ሥራዎች በአሁኑ ወቅት በወር ውስጥ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ቁጠባ የመሰብሰብ አቅም ላይ መደረሱ ተጠቁሟል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ቱሪ እንደገለጹት “ይህ ውጤት የገንዘብ ስኬት ብቻ ሳይሆን ደንበኞቻችን በእኛ ላይ ያላቸው እምነት ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

የድጋፍ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ምርቱ ከበደ በበኩላቸው፣ ተቋሙ በአዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ሀዋሳ እና አዳማ የሚገኙ 8 ቅርንጫፎች ቢኖሩትም፣ አገልግሎቱ ግን በመላ ሀገሪቱ ተደራሽ መሆኑን ገልጸዋል።

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የዞን እና የወረዳ ከተሞች የተሰማሩ ከ300 በላይ የሙሉ ጊዜ የብድር መኮንኖች እና ኤጀንቶች አሉት።

የአሠራር ዘይቤ፦ ደንበኞች ከሥራ ገበታቸው ሳይነቀሳቀሱ ባሉበት ሆነው በዲጂታል አማራጭ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል።

ተቋሙ የሰበሰበውን ተቀማጭ ገንዘብ መልሶ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ለደመወዝ ከፋዮች እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ለተሰማሩ የንግድ ዘርፎች በብድር መልክ በማቅረብ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን እያገዘ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
#digafmfi #ethiopiafinance #microfinance #digitalbanking #financialinclusion #trustandgrowth

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.