በጣሊያን አነጋጋሪ የሆነው "የሜሎኒ መልክ ያለው መልአክ" ተፋቀ!
በጣሊያን ሮም በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኝ የመልአክ ስዕል (Fresco) የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒን እንዲመስል ተደርጎ መሳሉ ታላቅ ውዝግብ አስነሳ።
የታሪኩ ዝርዝር፦
ክስተቱ፦ በቅዱስ ላውረንስ ባሲሊካ ውስጥ የሚገኝ የመልአክ ስዕል እድሳት ሲደረግለት፣ መልኩ የ49 ዓመቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒን ፍጹም በሚመስል መልኩ ተቀይሮ ተገኝቷል።
ተቃውሞው፦ ይህ ድርጊት በፖለቲከኞች እና በሀይማኖት መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። የሮም ሀገረ ስብከት የሆኑት ካርዲናል ባልዶ ሬይና "የክርስትና ጥበብ ለፖለቲካ መጠቀሚያ መሆን የለበትም" ሲሉ አውግዘዋል።
የተወሰደ እርምጃ፦ በካህናቱ ትዕዛዝ መሰረት የስዕሉ ፊት ዛሬ እንዲፋቅ ተደርጓል። ሰዓሊው ብሩኖ ቫለንቲኔቲ በቫቲካን ትዕዛዝ መሰረት ፊቱን ማጥፋቱን ገልጿል።
ምክንያቱ፦ የቤተክርስቲያኑ ፓስተር ዳኒኤል ሚኬሌቲ ሲናገሩ "ሰዎች ጸሎት ከማድረስ ይልቅ ስዕሉን ለማየት መሰለፋቸው ተቀባይነት የለውም" ብለዋል።
ሜሎኒ ምን አለች? 🤷♀️
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በኢንስታግራም ገጿ ላይ የስዕሉን ፎቶ በመለጠፍ "አይ፣ እኔ በእርግጠኝነት መልአክ አልመስልም" በማለት ነገሩን በፈገግታ አልፋዋለች።
የጣሊያን የባህል ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

4 months ago