Logo
Getu Temesgen
🎭 ቴአትር ወደ ደጃችን! አቃቂ ቃሊቲ ለኪነ-ጥበብ ድግስ ተዘጋጀች!

​#ethiopia | ተወዳጇ አርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ ደበበ እና የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቴአትርን ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ተስማሙ

​ቴአትርን ከመሀል ከተማ በማውጣት ወደ ነዋሪው ደጅ ለማምጣት የተደረገ "ይበል" የሚያሰኝ ጅምር!

​ዛሬ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከ "ባኪ የባህልና የኪነ-ጥበብ ማዕከል" (ህዳሴ የቴአትር አዳራሽ) ጋር በመሆን፤ ከአራዳ ፍሌክስ ኢንተርቴይመንት ምክትል ስራ አስኪያጅ አርቲስት ህብረ ቀለመወርቅ ደበበ ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

​የስምምነቱ ትሩፋቶች:
✅ ተደራሽነት: የአካባቢው ነዋሪዎች አዳዲስ ፊልሞችን እና ቴአትሮችን ለማየት ወደ ሩቅ መሄድ ሳይጠበቅባቸው በቅርበት ያገኛሉ።

✅ ጥራት: በብሔራዊ ቴአትር እና በሲኒማ ቤቶች እየታዩ ያሉ ምርጥ ስራዎች በታዋቂ አርቲስቶች ታጅበው ይቀርባሉ።

✅ ባህል: የቴአትር ባህልን በሰፊው በማዳረስ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል።

​ህብረ ቀለመወርቅ እና የአቃቂ ቃሊቲ አስተዳደር ለዚህ በጎ ጅምር ምስጋና ይገባቸዋል! በርቺልን! 🙏

​#theater #akakikality #hiberkelemework #art #cinema #ethiopia #culture #bakicenter #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.