Logo
FastMereja
ወርዶይ ሀኮ ይላል የሀገሬ ሰው....

ማንነቴን የሰራው ይህ ማህበረሰብ ነው!

እኔነቴን እንጀራዬን ከፈጣሪ በታች የሰጠኝ ይህ ማህበረሰብ ነው!

ምድር ላይ ዕድለኛ ከሆንኩባቸው እና ፈጣሪ ከማመሰግንባቸው ትላልቅ ዕድሎቼ መካከል የምወደው ከዚህ ማህበረሰብ መፈጠሬን ነው!

ሁሉም የዶርዜ እናቶች እናቶቼ ናቸው!

ቤቴ በእንግዳ የሚሞላው ከሁሉ በላይ እኝህን እናቶችን ብሎ ነው!

ትላንት የተፈጠረውን ነገር እና እውነታውን ላጠራላቹ እፈልጋለሁ እና እባካቹ ከስሜት ወጥታቹ ይህንን ጽሁፍ አንብቡልኝ።

ታዋቂው ቲክቶከር አዶናይ በቤቴ መጥቶ ተስተናግዶ የጋሞን ባህል አውቆ ስለተለያዩ የጋሞ ማህበረሰብ ትውፊቶች ተረድቶ እና በዶርዜ እናቶች ተደስቶ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

ታድያ በዚህ መሐል በተዝናኖት ላይ ሳለ መጠጥ ጠጥቶ የማያውቅ ልጅ እንደመሆኑ ለዶርዜ እናቶች 100 ሺህ ብር ሰጣቹሀለሁ ሲለኝ እኔ ደሞ ስላላመንኩት ምን አልባት በሞቅታ ተናግሮ ገንዘቡን ሳይሰጥ ከቀረ እናቶች ያንን ገንዘብ ስለሚጠብቁ ለሞራላቸው በማሰብ ብቻ ትርጓሜውን በሌላ ገልጬላቸው ነበር።

ነገር ግን ብሩ በትክክልም አዶናይ ሲያበረክትልኝ ገንዘቡን በአግባቡ ለእናቶች አከፋፍዬላቸዋለሁ።

ይህን ማረጋገጥ የሚፈልግ በምስሉ ላይ የሚታዩትን እናቶች ዶርዜ ድረስ መጥቶ መጠየቅ እና እውነታውን ማረጋገጥ ይችላል።

ሌላው ነገር እስከዛሬ ድረስ እኝህ እናቶች የቆዩት ከእኔ ጋር ነው። ወደ ፊትም የሚቆዩትም ከእኔው ጋር ነው። ቋሚ ደሞዝ ያላቸው ከተለያዩ የአለም ክፍላት የሚመጡ እንግዶችን ተቀብለው የሚያዝናኑ እና ባህላዊ ትውፊቱን የሚገልጹ እናቶት ናቸው።

ሰላም ለሀገራችን ይሁን!
ሞኬ ዶርዜ 👏👏

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.