Logo
Getu Temesgen
🐎​አጅባር ከሜዳው ስር እትብቴ ተቀብሮ፣
ደብረ ታቦር ያድራል ልቤ ዞሮ ዞሮ

* ከአጅባር ሜዳ እስከ ዴንሳ ግርጌ... ሰማይና ምድሩ የደመቀበት የቅዱስ መርቆሬዎስ ንግሥ! ⛪️🇪🇹
#ethiopia | ​ዛሬ የደቡብ ጎንደር ምድር በልዩ ድምቀት ታጅባ ዋለች። በታሪካዊቷ ደብረ ታቦር (አጅባር) እና በአምሳለ-አንበሳው እስቴ (ዴንሳ) ግርጌ የተከበረው የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል፤ ኢትዮጵያዊነትን፣ ጀግንነትንና እምነትን አስተሳስሮ አሳይቷል።

​📍 ደብረ ታቦር - አጅባር ሜዳ

ምድሩ በጀግኖቹ የፈረስ ግልቢያ ሲናወጥ፣ ሰማዩ በምስጋና እና በዘመናዊ የአየር ትርኢት ደምቆ ታይቷል። የበጌምድር መገለጫ የሆኑት ፈረሰኞች የሽምጥ ግልቢያ እና የጦር ውርወራ ጥበባቸውን ሲያሳዩ፤ የቀደሙት ነገሥታት ታሪክ በህያውነት ተመስሏል። ነዋሪዎቹም "እልፍኙ ተውቦ ነጭ ጤፍ እንጀራ እየተጋገረ" እንዲሉ፤ እንግዳን በክብር ተቀብለው አስተናግደዋል።

​📍 እስቴ - የዴንሳ ግርጌ

"የአንች ሀገር ወዴት ነው የእኔስ ሀገር እስቴ" የተባለላት እስቴ መካነ ኢየሱስ፤ ከ8 የፈረስ ማኅበራት በተውጣጡና "ፈረስ እንደ አሞራ" በሚያበሩ ጀግኖች ተሞልታለች። ከባለግርማው ዴንሳ ተራራ ግርጌ የታየው ትዕይንት ለዓይን የሚማርክ ነበር።

​ዛሬ ፈረሰኛው ፈረሰኛውን ሰማዕት (ቅዱስ መርቆሬዎስን) አጅቦ፤ ጥርን በድምቀት ሸኝቷል።

​ይህቺ ናት አገሬ፤ ይህቺ ናት ኢትዮጵያ! 💚💛❤️

​#debretabor #ajbar #este #densa #stmerkorios #gugs #culture #ethiopia #amhara #tourism #tradition #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.