የሶርያ መንግስት እና የኩርድ ታጣቂዎች ውህደት ሊመሰርቱ ነው
#ethiopia | በሶርያ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን አለመረጋጋት ለመቋጨት ይረዳል የተባለ "ታሪካዊ" ስምምነት በሽግግር መንግስቱ እና በኩርድ የሚመሩት የሶርያ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች (SDF) መካከል ተፈረመ።
የስምምነቱ ዋና ዋና ነጥቦች
* የጦር ሃይሎች ውህደት፦ የሶርያ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች (SDF) በሂደት በሀገሪቱ ብሄራዊ ጦር ስር እንዲካተቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ይህም በሀገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሀይሎችን ወደ አንድ ማዕከላዊ እዝ ለማምጣት ያለመ ነው።
* የድንበር ቁጥጥር፦ የፌዴራሉ መንግስት ሶርያን ከኢራቅ ጋር የሚያዋስነውን ስትራቴጂካዊ የሲማልቃ የድንበር ኬላ ለመቆጣጠር ከስምምነት ደርሷል።
* ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ፦ አሜሪካ እና ሌሎች አለምአቀፍ ተዋናዮች ስምምነቱን "ታሪካዊ እምርታ" ሲሉ አወድሰውታል።
ከውጥረት ወደ ሰላም
የኩርድ ታጣቂዎች የቀድሞውን የበሽር አል አሳድ መንግስት ለመጣል ከመሀመድ አልሻራ ጋር በጋራ ቢታገሉም፣ ከድሉ በኋላ ግን "ጥቅማችን አልተከበረም" በሚል ቅሬታ ገብተው ወደ ዳግም ግጭት አምርተው ነበር። አሁን የተደረሰው ስምምነት ግን ይህንን ቅሬታ በመፍታት ለሶርያ አንድነት እና መረጋጋት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎ ታምኖበታል።
ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚታየው ምስቅልቅል ፖለቲካ እንደ መልካም ተሞክሮ ተወስዷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #syria #sdf #peaceagreement #middleeastnews #syriatransition #kurdishforces #globalpeace

4 months ago