ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ቅርንጫፉን በይፋ አስመረቀ
#ethiopia | በምስራቅ ኢትዮጵያ በፋይናንስ ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ አሻራ በማሳረፍ የሚታወቀው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ፣ አገልግሎቱን ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ በማስፋት የመጀመሪያ የሆነውን የቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ በዛሬው ዕለት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ።
ተቋሙ አዲስ አበባን ጨምሮ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በጅግጅጋ እና በሀሮማያ ከተሞች ተደራሽነቱን በማስፋት፣ ለህብረተሰቡ የፋይናንስ አገልግሎትን በእኩልነት ለማዳረስ እየሰራ መሆኑ በምረቃው ላይ ተገልጿል።
በተለይም በትልልቅ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት ማግኘት ለሚቸገሩ እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች ተመጣጣኝ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት መስጠትን ዋነኛ ተልዕኮው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ እንደተገለጸው፣ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአሁኑ ወቅት አስደናቂ የፋይናንስ አፈጻጸም እያስመዘገበ ነው ተብሏል።
በምረቃውም ስነ ስርዓት ላይ
* ከ1.7 ቢሊየን ብር በላይ የብድር ክምችት
(Total Loan Outstanding) እንዳለው፣
* ከ111 ሺህ በላይ የቁጠባና የብድር ደንበኞችን ማፍራቱን፣
* የተቋሙ አጠቃላይ ካፒታል ከ677 ሚሊየን ብር በላይ መድረሱ ተመላክቷል።
በተለይም በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ እንደ ትልቅ ስጋት የሚታየው ለአደጋ የተጋለጠ ብድር (PAR) መጠንን ወደ 0.73% ዝቅ ማድረግ መቻሉ፣ የተቋሙን አስተማማኝነት እና የብድር አሰጣጥ ጥራት የሚያሳይ እንደሆነ ተብራርቷል።
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከመደበኛ የብድር እና ቁጠባ አገልግሎት በተጨማሪ፤ የህብረተሰቡን እሴት ያገናዘበ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት፣ የማሽነሪ ሊዝ፣ እንዲሁም እንደ ንጹህ ኢነርጂ (Clean Energy) እና ውሃና ሳኒቴሽን (WASH) ላሉ ዘርፎች የብድር አገልግሎት በመስጠት በፈጠራ ታግዞ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
አዲሱ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍም ፣ ለወጣቶች፣ ለሴቶች እና ለአነስተኛ የንግድ ስራ ፈጣሪዎች የስኬት በር እንደሚሆን በምረቃው ላይ መልዕክት ተላልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #diremicrofinance #financialinclusion #newbranch #addisababa #bolemichael #ethiopia #microfinance #economicempowerment #ድሬማይክሮፋይናንስ #ፋይናንስ #አዲስአበባ

6 months ago