ያንጎ፣ አካባቢያዊ ሥነ ምኅዳሩን ለማጠናከርና ተደራሽ ለመሆን የፍራንቻይዝ አጋር ግንኙነቱን በኢትዮጵያ አስፋፋ!
…
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ጥር 22 ቀን፣ 2018ዓ.ም.: ያንጎ ኢትዮጵያ፣ የፍራንቻይዝ አጋር ግንኙነቱ ላይ ሰፊ የማስፋፊያ ሥራ መሥራቱንና፣ ከአንድ ወደ ስምንት ንቁ የፍራንቻይዝ አጋሮች ማደጉን የገለፀ ሲሆን ይህም ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ፣ አካታች የሆነ እና በአካባቢው የሚመራ ጠንካራ የሥነ-ምኅዳር እንቅሳቃሴ ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ተገልጿል።
ማስፋፊያው፣ ያንጎ የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎችን ለማጎልበት፣ የጋራ ትራንስፖርት አገልግሎት ባለቤትነትን ሙያዊ ለማድረግ እና ሀገሪቱ እያስመዘገበችው ባለው ፈጣን የዕድገት የእንቅስቃሴ ዘርፍ ውስጥ በርካታ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማስፋት የነደፈውን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ያሳያል።
በተስፋፋው የፍራንቻይዝ ሞዴል መሠረት፣ ሹፌሮች እና ሞተረኞች በተመሳሳይ የያንጎ ፕላትፎርም ሥር ሆነው ግን ደግሞ ከአንድ በላይ ከሆኑ የያንጎ ፍራንቻይዝ አጋሮች ጋር ለመሥራት ዐመቺ አሠራር ተዘርግቶላቸዋል፡፡ ይህ አሽከርካሪዎች እና ሞተረኞች የደንበኞችን አገልግሎት ሳያስተጓጉሉ፣ በግል ፍላጎቶቻቸው፣ ምርጫዎቻቸው እና ሙያዊ ግቦቻቸው ላይ ተመሥርተው ሽርክናዎችን እንዲመርጡ፣ እንዲቀይሩ ወይም አጣምረው እንዲሠሩ ያስችላቸዋል፡፡
የፍራንቻይዝ ኔትወርክ ዕድገቱ እንዳለ ሆኖ ያንጎ ለተጠቃሚዎቹ እንደ አንድ ወጥ መድረክ ማገልገሉን ይቀጥላል፡፡ ሁሉም የፍራንቻይዝ አጋሮች የያንጎን፣ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት፣ ደኀንነት እና የአገልግሎት ፖሊሲዎች በማክበር መሥራታቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን ይህም በመላዋ ኢትዮጵያ፣ ለሁሉም ማለትም ለተሳፋሪዎች እና አጋር ሾፌሮች እና ሞተረኞች ወጥ የሆነ አስተማማኝ አገልግሎትን ለመስጠት ይረዳል፡፡
እያደገ ያለው የሥራ ግንኙነት፣ በፍራንቻይዝ አጋሮች መካከል ጤናማ ውድድርን በማስተዋወቅ ሾፌሮች እና ሞተረኞች በየጊዜው የተለየ ዋጋ እና ዕይታ ያላቸውን ሐሳቦች እንዲያቀርቡ ያበረታታል። እነዚህ አዳዲስ ሐሳቦችም፣ የአገልግሎት ሰጪዎችን እርካታ እና የረጅም ጊዜ ተሳትፎን የበለጠ ለማሳደግ የጋራ ትራንስፖርት ፋይናንስ አማራጮችን፣ የተግባር ድጋፍን፣ የማበረታቻ መርሐ ግብሮችን፣ የንግድ ሽርክናዎችን እና ዕውቅና ፕሮግራሞችን ሊያካትቱ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ የያንጎ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር የቀናለም አበበ “የፍራንቻይዝ አጋር ግንኙነታችንን ከአንድ ወደ ስምንት ስናስፋፋ፣ ከዚህም በላይ ሊሰፋ የሚችል እና የማይበገር ተንቀሳቃሽ ሥነ-ምኅዳርን በኢትዮጵያ ለመገንባት አቅደን ያደረግነው እርምጃ ነው። ከብዙ ኢትዮጵያውያን የንግድ ድርጅቶች ጋር በመሥራት እና አሽከርካሪዎች እና ሞተረኞች ከበርካታ የፍራንቻይዝ አጋሮች ጋር በአንድ የተዋሐደ መድረክ እንዲሠሩ በማመቻቸት የበለጠ ተለዋዋጭ፣ ጠንካራ ፉክክር እና ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድልን እየፈጠርን ነው። ይህ ዓይነቱ አሠራር፣ ለደንበኞቻችን ወጥነትና ጥራት ያለውን አገልግሎት የደህንነት ደረጃዎችን በመጠበቅ እንድናደርስ ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ የጥምር ትራንስፖርት አገልግሎትን በሙያ ለመደገፍ ያስችለናል።” ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡
የገበያ ጥናት (ምልከታ) እንደሚያሳየው የባለብዙ አጋር ፍራንቻይዝ ሞዴል ለተሻሻሉ የአሽከርካሪዎች እና ሞተረኞች ግንኙነቶች እና የሥራ እርካታ ትልቅ ሚና የሚኖረው ሲሆን በአዲስ አበባ እና ሌሎች የከተማ ማዕከላት እየጨመረ የመጣውን የትራንስፖርት አገልግሎት ፍላጎትን በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ አማራጮችን በዘላቂነት ለመጨመር ያስችላል።
ማስፋፊያው፣ ያንጎ ከተጨማሪ ኢትዮጵያዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የግብይት እና የፋይናንስ አቅርቦትን ከሚያመቻቹ ድርጅቶች እና መሰል ካምፓኒዎች ጋር ለመሥራት ያለውን ተነሣሽነት ያሳያል፡፡ ይህንን የፍራንቻይዝ ኔትዎርክ ያለማቋረጥ በማሳደግ፣ ያንጎ ከሰፋፊ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ግቦች ጋር የሚስማማ፣ ጠንካራ እና ግልጽ የሆነ የእንቅስቃሴ ስነ-ምህዳር በመገንባት የሀገር ውስጥ ሥራ ፈጠራን ለመደገፍ ዕቅድ ይዟል።
በዚህ ተነሳሽነት፣ ያንጎ የሀገር ውስጥ ቢዝነሶችን ለመደገፍ፣ ለአጋር ሾፌሮች እና ሞተረኞች ተጨማሪ የገቢ ዕድሎችን ለመፍጠር እና አስተማማኝ የትራንስፖርት አገልግሎትን በአንድ እና በተቀናጀ መድረክ ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች ለማድረስ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።
https://yango.com/en_et/dr...
###
ስለያንጎ ግሩፕ
ያንጎ ግሩፕ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱን በዱባይ ያደረገ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ዕለታዊና ኑሮን የሚያቀሉ አገልግሎቶች በመቀየር ማኅበረሰቦችን የሚያገለግል ተቋም ነው። ለፈጠራ ባለው የማያወላውል ቁርጠኝነት፣ ከዓለም ዙሪያ መሪ ቴክኖሎጂዎችን ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያለምንም እንከን ወደ የተቀናጀ የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች ይቀይራል፤ በየጊዜውም ያዘምናል፡፡
የያንጎ ባለብዙ-ተግባር መተግበሪያ በአፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ባሉ ከ20 በላይ ሀገራት ውስጥ በርካታ የዲጂታል ከተማ አገልግሎቶችን ይሰጣል። የያንጎ ብዙ ቋንቋ ተናጋሪ መተግበሪያ በአንድሮይድ እና አይኦኤስ ላይ በነጻ ይገኛል።

4 months ago